Prosperity Party

ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ መጋቢት 01/2018 ዓ.ም ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት አደጋ የህይወት እና የንብረት መጥፋት ላጋጠማቸው ዜጎች የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የበልግ ዝናብ እየዘነበ ይገኛል፡፡ በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች ከበድ ያለ ዝናብም ተስተዉሏል፡፡ ለአብነትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ የተከሰተዉ የመሬት መንሸራተት የተፈጥሮ አደጋ በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ መጋቢት 01/2018 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በደረሰዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለደረሰዉ የዜጎቻችን ህይወት መጥፋት ብልፅግና ፓርቲ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ዜጎች ቤተሰቦቻቸዉና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ 

እየዘነበ ባለዉ ዝናብ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለዉን ጉዳት ለመቀነስ የአካባቢዉ አስተዳደርና ህብረተሰቡ ልዩ ክትትልና ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ እናስተላፋለን፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party