Prosperity Party

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ለአቶ አደም ፋራህ በጽ/ቤታቸው አቀባበል አደረጉ

ጥር 05 2018 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (/) ለብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ለፓርቲው ዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ አቀባበል አድርገዋል።

አቶ አደም ፋራህ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃውን የርዕሰ መስተዳድር /ቤት፣ ቤተ መንግስት እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ህንጻዎችን ተመልክተዋል።

ከፍተኛ አመራሮቹ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያቀኑት በነገው ዕለት በሆሳዕና ከተማ በሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ 6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ ላይ ለመገኘት ነው።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ምልከታ አድርጓል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party