የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና ክላስተሮችንና ሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።
ሰልጣኞቹ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ በክላስተር እየለማ ያለውን የፓፓያ ማሳ ተመልክተዋል፡፡
በክላስተር እየለማ ያለው እና “red ready" የሚባለው የፓፓያ ዝርያ ከአንድ ዛፍ ላይ እስከ አንድ ኩንታል ምርት ሊያስገኝ እንሚችል በምሥራቅ ሸዋ ግብርና ቢሮ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
አመራሮቹ በዞኑ ሉሜ ወረዳ በክላስተር እየለማ ያለውን የዓሣ ምርትም የጎበኙ ሲሆን፣ በክላስተር እየለማ ያለው ዓሣ አመራረት ትምህርት የሚወሰድበት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በሉሜ ወረዳ ቆቃ ባና ቀበሌ ለ80 ወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረው የዓሣ ማርቢያ ፖንድም ሌሎች ክልሎች ጥሩ ተሞክሮ ያዩበት መሆኑ ተገልጿል።
በገጠር ትራንስፎርሜሽን ከማምረት ለውጪ ገበያ እስከማቅረብ የዘለቀ መሆኑንም ተብራርቷል፣ ገጠሩን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ገጠሩን እና ከተማውን ለማስተሳሰር የተሄደበት ርቀት በጎ ጅምሮች መኖራቸው ተመልክቷል፡፡