በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅ/ፅ/ቤት የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም አካሄደ
በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅ/ፅ/ቤት የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም አካሄደ
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫ የዴሞክራሲያ ስርዓት ግንባታ መሰረት የሚጣልበት ፣ የህዝብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጥበት በመሆኑ ፍትሀዊ ፣ ገለልተኛ ፣ የህዝብ ድምፅ የሚከበርበት እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥተው እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህዝባችን በድምፁ መንግስትን የመመስረት ሉዓላዊ ስልጣኑን መጠቀም የቻለበት መሆኑን ያወሱት ክቡር ፕሬዝዳንት የተጣለውን መሰረት ይበልጥ በማፅናት ዴሞክራሲን ለመገንባት ለ7ኛው ከተማዊና ሀገራዊ ምርጫ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው ሀገር በቀል በሆነው የመደመር እሳቤ የተመራው ብልፅግና ፓርቲ በቃሉ በመታመን ሀገራዊ ድሎችን ማስመዝገቡን ጠቅሰው በተመዘገበው አንፀባራቂ ስኬት የህዝባችን እምነት መለምለሙን አስረድተዋል።
በያዝነው ዓመት ክልላችን ብሎም ሀገራችንም ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን መሸጋገራቸውን ያወሱት ኃላፊው ሀገራችንንም የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተቀመጠው ግልፅ ራዕይ ዕውን እንዲሆን በእሳቤዎች የተቃኘ በተግባራዊ ውጤታማነት የታጀበ ማኒፌስቶ በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉን ገልፀዋል።
በሁሉም መስክ ፀጋዎቿን በማልማት የጠንካራ ሀገር ተምሳሌትነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል የተመላከተ ሲሆን ፤ በትብብር እና በፉክክር መካከል ያለውን ሚዛን የሚጠብቅ በመግባባት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲ የመገንባት ርብርቡ ይበልጥ እንደሚጎለብት በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል።
በፕሮግራሙ ላይ የፓርቲያች ማኒፌስቶ ይፋ የተደረገ ሲሆን የመደመር ፣ የብልፅግና ፣ የልዕልና ትርጉም ያለው የብልፅግና ፓርቲ መለያ ምልክት የሆነው የስንዴ ነዶ በታላቅ ድምቀት ተዋውቋል።
ዛሬ የካቲት 10/ 2018 ዓ.ም በተካሄደው በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅ/ፅ/ቤት የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቅያ ፕሮግራም ከፍተኛ አመራሮች ፣ የፓርቲያችን አባላት ፣ ደጋፊዎች እና ልዩ ልዩ የህብረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።