You are currently viewing አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሄደ

አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሄደ

  • Post comments:0 Comments
አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሄደ
በአንደኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የተመረጠው የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን የፓርቲው ጉባዔ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው የጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት እቅድ ተዘጋጅቶ ውሳኔዎቹና አቅጣጫዎቹ በፍጥነት መተግበር እንዲጀምሩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ኮሚቴው በተጨማሪም አዲስ የተገነባውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የመረቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችንም በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡

ምላሽ ይስጡ