You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው

  • Post comments:0 Comments
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ እየጎበኘ ነው።
በጉብኝቱም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉብኝቱ ላይ ፥ ከዚህ በፊት የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የግብርና ልማታችን የእድገታችን መሰረት ስለሆነ ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ያሉ ሲሆን፥ በግብዓትና በገበያ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመለስ አብዲሳ ፥ዘንድሮ በክልሉ ከሚመረተው የስንዴ ምርት ውስጥ 74 በመቶ በኩታ ገጠም የሚመረት ነው ማለታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ምላሽ ይስጡ