በወራሪው የህወሓት የሽብር ቡድን የተያዙ የአማራ ክልል ቦታዎችን በአጠረ ጊዜ ነፃ ለማውጣት እንደሚሰሩ አዲሱ የአማራ ክልል ር/መስተዳድር ገለፁ
በወራሪው የህወሓት የሽብር ቡድን የተያዙ የአማራ ክልል አካባዎችን በህልውና ዘመቻው በአጠረ ጊዜ ነፃ ለማውጣት በትኩረት እንደሚሰሩ አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፍለ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ብህልውና ዘመቻው ወራሪውን ቡድን አቁስሎ መተው ብቻ ሳይሆን ስጋት እንዳይሆን አድርጎ መተው ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳደሩ ለአማራ ክልል ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል፡፡
የወራሪው ቡድን በሰሜን ወሎ፣ዋግ ኸምራ እና ሰሜን ጎንደር ወረራውን በመፈፀም የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር ያደረገውን ጥረት መላ የክልሉ ህዝብ በአንድነት በመቆም ህልውናውን ለማስከበር አኩሪ ጀብዱ በመፈፀም አንድነቱን አሳይተዋል ብለዋል፡፡
ወራሪው የሽብር ቡድን እየፈፀመ ያለው ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል እና ንብረት ማውደም የአማራ ክልል ህዝብ አንድነት እንዲቆም ከማድረጉ ባሻገር፣ የኢትዮጰያን አንድነት ለማስከበር የቆመ መሆኑን በዘመቻ ህልውናው በግልፅ ማሳቱንም ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፍአለ /ዶ/ር/ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ህዝብ ህልውና እና ክብር የሚረጋገጠው ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆኑ ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ ክልሉ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
የዘመቻ ህልውናውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣
ተፈናቃዮችን ለማቋቋምም እና ድጋፍ ለማድረግ አዲሱ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡