You are currently viewing በ76ኛው የተመድ ጉባኤ በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አደረገ

በ76ኛው የተመድ ጉባኤ በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አደረገ

  • Post comments:0 Comments
በ76ኛው የተመድ ጉባኤ በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አደረገ
በ76ኛው የተመድ ጉባኤ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከተለያዩ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ባደረጉት ውይይት በህዳሴ ግድቡ እና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል፡፡
በሃገራት ላይ እየተደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት እንዲቆም የጠየቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ አሸባሪው የህውሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ባለው ሰብዓዊ ቀውስ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ከተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ለዲፕሎማቶች በተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ አለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች በጥናታዊ ስራዎች ተደግፈው ቀርበዋል፡፡
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አድሎአዊ ዘገባ እያሰራጩ ያሉ አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማትን በሲ ኤን ኤን ዋና ማሰራጫ ፊት ለፊት ተሰብስበው አውግዘዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ