You are currently viewing አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ነው፤ ሚዛን አልባው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል

አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ነው፤ ሚዛን አልባው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል

  • Post comments:0 Comments
አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ነው፤ ሚዛን አልባው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል
አሸባሪው የህወሓት ቡድን የግራይ ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ እንደሆነ የሚወጡ የምስል ማስረጃዎች እያሳዩ ነው። በተቃራኒው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል።
በዓለም አቀፍ ህግ ህጻናትን ለጦርነት መጠቀም ወንጀል መሆኑ እየታወቀ ራስ ወዳዱ ጁንታ እድሜያቸው ለትምህርት እንጂ ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን በሀሽሽ አደንዝዞ ጦርነት ውስጥ እያሰለፈ ነው።
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንም ጉዳዩን በራሳቸው ዘገባ ጭምር ይዘው ቢወጡም ጉዳዩን ከማውገዝና አጥፊዎችን ከመኮንን ይልቅ በተቀራኒ ተሰልፈው የጁንታው ወንጀል አስተባባዮች ሆነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል” ሲሉ የጉዳዩን አደገኛነት አስታውቀዋል።
የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በሁዋላ የህግ ማስከበር ዘመቻው ሲፋፋምባቸው የትግራይ ህጻናት ድንጋይም ቆንጨራም በመያዝ እንዲታገሉ ጥሪ ማድረጉ አይረሳም። አሁንም በተጨባጭ እየሆነ ያለው ይሄው ነው።
ዓለም፤ “…ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን የገለጹት፤ አሁን ለጁንታው የተሰጠው እድል የመጨረሻ የሰላም አማራጭ መሆኑን በመጥቀስ ነው።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከተለያዩ ማህበራዊ ገጾች እና ከራሱ ከጁንታው ደጋፊዎች ገጾች የሰበሰባቸውን የህጻናት “ወታደሮች” ምስሎችን እንዲህ አቅርቧቸዋል።

ምላሽ ይስጡ