You are currently viewing የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በአፋር ላይ የከፈተውን ወረራ የሚያወግዙ ህዝባዊ ሰልፎች በአፋር በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች ተካሂደዋል

የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በአፋር ላይ የከፈተውን ወረራ የሚያወግዙ ህዝባዊ ሰልፎች በአፋር በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች ተካሂደዋል

  • Post comments:0 Comments
የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በአፋር ላይ የከፈተውን ወረራ የሚያወግዙ ህዝባዊ ሰልፎች በአፋር በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች ተካሂደዋል።
የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በአፋር በአርብቶ አደሩ ህዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚያወግዙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፎች በአፋር በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በዛሬው እለት ተካሂዷል።
ሰልፈኞቹ በአፋር ህዝብ ላይ ጁንታው የከፈተው ጦርነት የአፋርን መሬት የራሱ ለማድረግና የአፋርን ህዝብ በቅኝ ግዛት ለመግዛት ካለው የማይሳካ ህልም በመነሳት መሆኑን ህዝቡ በሚገባ እንደሚረዳና ይህም ደግሞ ፈፅሞ ሊሳካ የማይችል ቅዠት መሆኑን በሰልፉ ገልፀዋል።
አያይዘውም ህዝቡ አሸባሪ ቡድኑን ለመመከትና ለማጥቃት ዝግጁ መሆኑንና ጁንታውን አሳፍሮ ለመመለስ ምንም የሚሰስቱት ነገር እንደሌለ ሰልፈኞቹ በመፈክራቸው አስታውቀዋል።
በአፋር ህዝብ እና መሬት ላይ ግልፅ ሽብር ያወጀውን በማንነታችን የመጣውን አሸባሪው ህወሓት የሚገባውን ለመስጠት አስፈለጊውን ሁሉ መስዋእትነት እንከፍላለን ሲሉ አረጋግጠዋል ።
የተቃውሞ ሰልፉ በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ህዝቦች የተሳተፉበት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አሸባሪው ህወሓት ያካሄደውን ወረራ ሰልፈኞቹ በማውገዝ የሽብር ቡድኑን ለመፋለምና ለመመከት ከዚህ ሰአት ጀምሮ ወደ ግንባር እንደሚሰለፉ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምላሽ ይስጡ