የመሠረት ድንጋይ ከተጣለበት እለት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሁሉም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከተማሪ እስከ ምሁሩ ድረስ ያለው በጉልበቱ፣ በገንዘቡና በዕውቀቱ ለመርዳት ቁርጠኝነቱን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወቅና ምናልባትም አለምን ያስደመመ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡
ከድህነት መውጫ መንገዶች አንዱና ዋነኛው መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ድረስ ተሳትፏቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል። የአገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ አንዱስትሪ ስለሚያሸጋግር ዜጎቿ ከዕለት ጉርሳቸው ቀንሰው ለማጠናቀቅ ከጊዜ ጋር እልህ ውስጥ ገብተዋል፤ይህ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ያለ የሁሉም ዜጎች አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነው፡፡
ግድቡ ኢትዮጵያ ያላትን አካባቢያዊም ሆነ አህጉራዊ አቅም እንደሚያጠናክርና ብሔራዊ ክብሯን እንደሚያስጠብቅ አጥብቀን ስለምንረዳ ኢትዮጵያዊያን ቀዳሚ ሀገራዊ አጀንዳችን አድርገን ይዘነዋል ። ግድቡ ለዜጎች ብሔራዊ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ይታወቃል።
ብልጽግና በመጨረስ እንጂ በመጀመር አያምንም፡፡ በብዙ ቢሊዬን ብር ወጪ የተጀመሩና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ በተለያዩ ጊዚያት በህዝብና በመንግስት የጋራ ትብብር በግንባታ ሂደት ውስጥ ያሉ በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ቢሆን ኖሮ እንደ ሀገር የኢኮኖሚውን አቅማችንን ያሳድጉት ነበር፡፡ስለሆነም ብልጽግና ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ የተጀማመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን የመጨረስና ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ላይ እንዲውሉ የርብርብ ማዕከል እንዲሆኑ ያደረገው፡፡
እንደ ገዢ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግስት በዋናነት ትኩረት ከተሰጣቸው ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አንዱ ነው፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያዊያን ያለው ትርጉም ከፍ ያለ ነው፡፡ ሀይል ከማመንጨት ባሻገር የመተባበር፣የአንድነት፣እርስ በእርስ ያለንን ግንኙነት ያጠናከረ፣ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያለንን ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችንን የበለጠ የሚያጎለብት እንዲሁም የይቻላል መንፈስን ያሣዬን ጭምር በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊያን በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከዚህ ቀደም ያደርጉት የነበረውን ድጋፍ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡
መሰረታዊ የሆኑትን እና ሃይል ከማመንጨት ባሻገር ግድቡ በግንባታም ሂደት ውስጥ ሆኖ ያስገኛቸው በርካታ ትሩፋቶች አሉ፤ የመጀመሪያውና መሰረታዊው ነገር እንደ ሀገር ብሄራዊ መግባባትን የፈጠረ ግድብ መሆኑ ነው። የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት እለት ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሁሉም ከልጅ እስከ አዋቂ ያሳየው ድጋፍ፣ የሃገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ያሳዩት ተነሳሽነት እና በግድቡ ዙሪያ የፈጠሩት አንድነት ከመቼውም በላይ እንዲቀራረቡ እና በጋራ እንዲረባረቡ ማድረጉ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር በየትኛውም ዘርፍ ለተያያዝናቸው አጀንዳዎች ትልቅ እና የገዘፈ ብሄራዊ አቅም ፈጥሮልናል፡፡
ሌላው ህዝቡ ስለአባይ ያለውን ቁጭትና ከሃይል የዘለለ ሉአላዊነትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መንግስት የማይደራደር እንደሆነ ስለሚገነዘብ መሆኑ አያጠያይቅም። ስለሆነም የመሰረት ድንጋዩ በኖረበት ማግስት ተጨማሪ ጥሪ ለህዝቡ ሳያስፈልግ በእልህ እና በቁጭት ተነስቷል። እንደ ህዝብ ለዘመናት ተጠናውቶን የነበረውን የተረጂነት እና የተመጽዋችነት መንፈስ ከጫንቃችን አሽቀንጥረን በመጣል የይቻላል መንፈስን ሰንቀን በተግባርም እንድናረጋግጥ ያስቻለን በመሆኑ ነው፡፡
በመሆኑም ለዚህ ግድብ ግንባታ ያለምንም የውጭ ድጋፍም ሆነ ብድር በራሳችን አቅም ተጠናክረን ግድቡን ዛሬ ላይ 80 በመቶ ማድረሳችን ለአፍሪካም ሆነ ዓለም ላይ ላሉ ሃገራት በራሳቸው አቅም ህዝባቸውን አስተባብረው ማደግ እንደሚችሉ ያሳየ የሰንደቅ ዓላማ ፕሮጀክታችን መሆኑን ተረድተን የኢትዮጵያዊያን የመልማት ጥያቄ የእግር እሳት የሆነባቸው ከውስጥም ሆነ ከውጭ ያሉ ሃይሎች ከልማት መንገዳችን ሊያስተጓጉሉን ይፈልጋሉና አንድነታችንን በማጠናከር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን በህብር ወደ ብልጽግና እናሻገር መልዕክታችን ነው፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ