You are currently viewing የሀገር ሉዓላዊነት…

የሀገር ሉዓላዊነት…

  • Post comments:0 Comments
የሀገር ሉዓላዊነት ከምንም ከማንም በላይ ነው፤ሉዓላዊነት በወሰን፣በሕግና በሃገር ጥቅም ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ መጠን በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መላው ኢትዮጵያዊያን በአንድ ልንቆም ይገባል፡፡ለዚህ ደግሞ ዋናው ጉዳይ ውስጣዊ አንድነታችንን መጠበቅና ክፍተት እንዳይፈጠር ማድረግ ነው፡፡
 
ከትንንሽ ልዩነቶቻችን ወጠን አንድ ወደሚያደርገን ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡በአገር ጉዳይ አንድ መሆን አለብን፡፡የጋራ መጠለያችን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡መጠለያ ከሆነችን ደግሞ አገራዊ ክብሯን፣ብሔራዊ ጥቅሟን፣ለጥያቄ የማይቀርበው ሉዓላዊነቷን ጠብቀን ልናስጠብቅ የግድ ነው፡፡
 
አገራዊ ሉዓላዊነት ትርጉሙ ምን ያህል ከፍ ያለ መሆኑን ከአባቶቻችን ተምረናል፡፡አባቶቻችን የጣሊያንን ወራሪ ሃይል መክተው የአገራቸውን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የቻሉት አንድ መሆን በመቻላቸው ነው፡፡ ነጻነት ክብራቸው፣አገራቸው መድመቂያቸው መሆኑን በውል በመረዳታቸው ነው፡፡
 
አንዳንዶቹ ምክንያታቸውን በዓባይ ውሃ ላይ አድርገው ጫና ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያል፤አልችል ያሉት ደግሞ በሃያላን አገራት ለማስፈራራት ይሞክራሉ፡፡ይህ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ በውስጥ ጉዳዮቻችን ጣልቃ በመግባት ልዩነት እንዲፈጠርና ወደ ማያባራ ግጭት ለማስገባት እንቅልፍ አጠው ይሰራሉ፡፡
 
ያም ሆነ ይህ አገራችን በአሁኑ ሰዓት ውስብስብና እጅግ ፈታኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ይህን ፈታኝ ወቅት ማለፍ የምንችለው ደግሞ ከራስ በፊት ለአገር ቆመን እንደ አባቶቻችን አንድነታችንን ስናጠናክር ብቻ ነው፡፡
 
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCDjrabrExOjDbogAkeOUI5w
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ