You are currently viewing ምክር ቤቱ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንዲካሄድና የኮቪድ 19 ወረሽኝን መከላከልን መሰረት ያደረገ የምርጫ ዝግጅት እንዲጀመር ውሳኔ አሳለፈ

ምክር ቤቱ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንዲካሄድና የኮቪድ 19 ወረሽኝን መከላከልን መሰረት ያደረገ የምርጫ ዝግጅት እንዲጀመር ውሳኔ አሳለፈ

  • Post comments:0 Comments

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንዲካሄድ እና የኮቪድ 19 ወረሽኝን መከላከልን መሰረት ያደረገ የምርጫ ዝግጅት እንዲጀመር ውሳኔ አሳለፈ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በዛሬው እለት አካሂዷል።በአስቸኳይ ስብሰባውም የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉደዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጤና ሚኒስቴር ሀገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ባቀረበው ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ላይ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በዝርዝር ተመልክቶ በአንድ ተቃውሞ፣ በስምንት ተአዕቅቦ፤ በአብላጫ ድምፅ አጽድቆታል።በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መከላከልን መሰረት በማድረግ ክልከላ የተጣለባቸው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲፈቀዱ እና ትምህርት ቤቶችም እንዲከፈቱ ሲል ነው ውሳኔ ያሳለፈው።እንዲሁም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንዲካሄድ የኮቪድ 19 ወረሽኝን መከላከልን መሰረት ያደረገ የምርጫ ዝግጅት አንዲጀመር ወስኗል።በውሳኔውም በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ማስፈጸሚያ መመሪያ እና አሰራሮችን በመዘርጋት፤ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ ወስኗል።

ምላሽ ይስጡ