You are currently viewing በተቻለ መጠን ጥያቄ አለኝ የሚል አካል በሙሉ የሚያነሳውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ በሆደ ሰፊነት መንቀሳቀስ ጀምረናል፡፡

በተቻለ መጠን ጥያቄ አለኝ የሚል አካል በሙሉ የሚያነሳውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ በሆደ ሰፊነት መንቀሳቀስ ጀምረናል፡፡

  • Post comments:0 Comments

በሀገራችን ካሉን ዕንቁ ሀብቶች አንዱና ዋናው ሰላማችን ነው፡፡ ጥንትም በፈሪሃ ፈጣሪ፣ በመቻቻልና በመተባበር እንዲሁም

በመተዛዘንና መረዳዳት የሚታወቀው ህዝባችን ለሰላም ቀናኢነት ያለውና የነበረው ነው፡፡

ኢትዮጵያ መላው የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመሰረቱት ህገ መንግሥታዊና ፌዴራላዊ ሥርዓት

እየተመሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም በሀገሪቱ እያቆጠቆጡ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና መሰል ልማታዊ እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ

አንድ እርምጃ ማሳደግ ተችሏል፡፡ ለዚህ ሁሉ መሰረታዊ እንቅስቃሴ ዋነኛው መሰረት ታዲያ ሰላም ነው፡፡

ሀገራችን አስከፊ ከሆነ ጦርነት ወጥታ አዲስ ምእራፍ ትጀምር ዘንድ ፓርቲያችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የሀገሪቱን ተስፋ እያለመለመ ያለውን ሠላም የሚያደፈርሱ ክስተቶች በአንዳንድ ቦታዎች እየታዩ ነው፡፡

በአንድ በኩል ህጋዊነት የተላበሱ የሚመስሉ የህዝብ ጥያቄዎችን ተንተርሶ፣ በሌላ በኩል በለየለት የፀረ ሰላምና የጥፋት ድርጊት

ውስጥ ተሰልፎ ከህግና ሥርዓት ውጪ የሚፈፀም ፀረ ዴሞክራሲያዊ ድርጊት ተደጋግሞ ታይቷል፡፡

መንግሥትም ሆነ ፓርቲያችን ብልፅግና ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ህዝብን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

በተቻለ መጠን ጥያቄ አለኝ የሚል አካል በሙሉ የሚያነሳውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ በሆደ ሰፊነት መንቀሳቀስ ጀምረናል፡፡

ከዛ ውጪ ያሉ አማራጮችን መርጦ ከሚንቀሳቀስ አካል ጋር ግን ህግ ማስከበር እና ህገ መንግስታዊ ግዴታችንን መወጣት

እንዳለብን ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ