የክልል እና ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የሲቪልና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ አመራሮች ጉብኝት አካሄዱ
በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሲቪልና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ አማካኝነት የተዘጋጀውና ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የዘርፉ አመራሮች፣ የፌዴራል እና የክልል የወጣትና የሴት ሊግ አመራሮች በተገኙበት በአዳማ እና በወንጂ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የሲቪልና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ግምገማ አንዱ አካል የሆነው የጉብኝት መርሐ ግብር ሲካሄድ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪው ህዝብ አማካኝነት የተሰሩ እና በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የብልጽግና ፓርቲ የሲቪልና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ አቶ ፓል ቶትን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የሲቪልና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ግምገማ በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡