ፅንፈኝነት ለማንም የማይበጅ የተሸናፊዎች መንገድ ነው፡፡ አሁን አገራችንን የሚበጀው በወንድማማችነት ስሜት ተደምሮ ወደፊት መገስገስ ብቻ ነው።
አብዛኞቹ ችግሮቻችን የጋራ መሆናቸዉን ተገንዝበን የጋራ መፍትሄ መፈለግ ይገባል፡፡
ኋላቀርነትን፣ ድህነትን፣ የተቋማት ድቀትን፣ ፅንፈኝነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትን እና ሌሎች መሰናክሎችን በማለፍ ወደ ብልፅግና መዝለቅ የምንችለዉ በመተሳሰብ እና በመተማመን አቅሞቻችንን ስንደምር ብቻ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ የወንድማማችነት እሴትን ማጎልበት ይገባል፡፡ ፅንፈኝነት እና ዋልታ-ረገጥነት የህብረት ክንዳችንን ከማዛል ባሻገር ሊያጠፋፋን ይችላል፡፡
የሁላችንም ጥቅም በወንድማማችነት ስንደመር ይከበራልና ወንድማማችነትን የሀገር ግንባታ መሠረት ልናደርገዉ ይገባል።