You are currently viewing ፕሮግራሞቹን በተግባር ማሳዬት የቻለ ፓርቲ – ብልጽግና

ፕሮግራሞቹን በተግባር ማሳዬት የቻለ ፓርቲ – ብልጽግና

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በልጆቿ ብርታት አጠናክራ ቀጥላለች፡፡በሃገራዊ አንድነት ጥላ ስር ተሰብስበን ለሃገራዊ ለውጥ የምንተጋበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ብልጽግና ፓርቲ ይህንን ቃል በመፈጸም በህዝብ ዘንድ የተጣለበትን እምነትና አደራ ለመወጣት እየተጋ ይገኛል፡፡
ብልጽግና ሕብረ-ብሔራዊ ሆና በተገነባች ኢትዮጵያ የወንድማማችነት እሳቤን በማስቀደም የአገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ዕውን ለማድረግ የኢኮኖሚ ፕሮግራሞቹን መሰረት ያደረገ ጥረት ላይ ይገኛል፡፡
የፓርቲው ፕሮግራም በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለተግባራዊነቱ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳዬ ይገኛል፡፡
ብልጽግና የኢትዮጵያዊነት ባህሪን የያዘ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ ይህ ማለት እርስ በእርስ መተሳሰብን፣ መተጋገዝን፣ አንድነትንና ወንድማማችነትን የመሰሉ የቆዩ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ለማስቀጠል የሚሰራ ወቅቱን የዋጀ ፓርቲ ነው፡፡
አመራሩም ሆነ አባሉ እነዚህን ኢትዮጵያዊ እሴቶች ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ አደራ ተጥሎበታል፡፡ ከእዚህ አኳያ አመራሩም ሆነ አባሉ የፓርቲውን ፕሮግራምና ህገ ደንብን ተከትሎ እየተመራ ጉዞዉን ቀጥሏል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጎልበት ድህነትን አሸንፎ እንደ አገር ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመፍጠር በልዩ ልዩ መስኮች ወደ ተግባር ከገባ ቆየት ብሏል፡፡ በግብርናው፣በሃይል አቅርቦት፣በአየር ትራንስፖርት፣በቡና፣በማዕድን ዘርፍ እና በመሳሰሉት ተጨባጭ አገራዊ ለውጥ ማምጣት ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ያዳበረውን ፍቅር፣ መከባበርና መደጋገፍ እንደገና ወደነበረበት በማስቀጠል አንዱ ጎታች ሌላው ተጎታች ሳይሆን ወይም አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆን ሁሉም እኩል ለሀገሩ ብልፅግና አሻራውን የሚያሳርፍበት ወቅት እንዲሆን ብልጽግና ከምንጊዜውም በላይ ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ከሰራቸው ስራዎችና ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ገና ወገብ የሚያጎብጡ ዘመን ተሻጋሪ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውጤት ለማምጣት ርብርብ እያደረገ የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡ ምክንያቱም ብልፅግና በዕውቀትና በዕውነት ላይ የቆመ ፓርቲ ነውና፡፡ ብልጽግና ህልሙ ትልቅና ሰፊ እንጂ በትንንሽ ነገሮች ረክቶ የሚቀመጥ ፓርቲ እንዳልሆነ ካስቀመጣቸው ፕሮግራሞችና ህገ ደንቦች መረዳት ይቻላል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ አጀንዳው ግልጽ ነው፤ሰላም፣ልማት፣ብልጽግና ናቸው፡፡እንዚህን አጀንዳዎቻችንን ለሃገርና ለሃገራዊ አንድነት ቅድሚያ በመስጠት የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ ድካማችን መገንባት እንችላለን፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ነገን ተሻግሮ ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ፓርቲው ለአገርና ለህዝብ የማይከፍለው መስዋዕትነት የለም፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ፕሮግራሞቹ ሰፊና እንደ አገር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ግቦችን አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል፡፡
#prospeirty

ምላሽ ይስጡ