የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ፕሮግራም ዓላማ፡-

የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ፕሮግራም ዓላማ፡-

  • Post comments:0 Comments
ሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት መነሻዋ ዝቅተኛ ደረጃ በመሆኑ ሁለንተናዊ ማህበራዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዳይ የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ፕሮግራም አንድ ዋና ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም የማህበራዊ ልማት ሥራዎቻችን የዕድገትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መንትያ ግቦችን የማሳካት ጉዳይ ይሆናል።
ማህበራዊ የልማት ሥራዎቻችን ከችሮታና ከነባሩ የማህበራዊ ደህንነት ትኩረት ወጥቶ ችግሩን ከመብት አንፃር እንደሚመለከተው ብልጽግና ፓርቲ በማህበራዊ ልማት ፕሮግራሙ ላይ በግልጽ አስቀምጧል። የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተደራሽነትና አካታችነት ባለው መልኩ የማህበረሰብን ጤና፣ ደኅንነት እና ምቾት የሚያስጠብቅ መሆን ይኖርበታል ብሎ ያምናል።
የብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ፕሮግራም ዜጎችን የሚያስተሳስር፣ ከችግርና ከመከራ የሚታደጋቸው፣ የሀገርን አለኝታነት የሚያሰርጽ እና በሀገራችን አዎንታዊ ሰላምን የሚያረጋግጥ ይሆናል። ማህበራዊ የልማት ፕሮግራሙ ህብረ ብሔራዊ ማንነትን መሠረት ያደረገ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብት እንዲሆን ኢላማ አድርጎ መንቀሳቀስ የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ፕሮግራም ዓላማ መገለጫ ነው።
ይህንን እውን ለማድረግ በማህበራዊ ልማት ዘርፍ የአርሶ አደሩን እና አርብቶ አደሩን፣ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የከተማ ነዋሪ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲ እየሰራ ይገኛል።
#prosperity

Leave a Reply