“መደመር” አገራችንን ወደ ለውጥ ጎዳና የሚመራ ፍኖተ ካርታ ነው፤
እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት በዓይን የሚታይ፣በእጅ የሚዳሰስ ለውጦችን በሁሉም መስኮች ማስመዝገብ መቻሏ የሚታወቅ ነው፡፡ይህ ደግሞ በመረጃ ብቻ ሳይሆን በማስረጃም ጭምር ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ኢትዮጵያ ሰፊውንና ፈጣኑን የለውጥ መንገዷን መነሻ አድርጋ መዳረሻዋን ከብልፅግና ማማው ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ከጊዜ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ገብታለች፡፡
ሀገር ሀገር ሆና ልታድግ የምትችለው የእያንዳንዳችን ዕውቀት፣ጉልበትና ገንዘብ ተደምሮ በምናበረክተው አስተዋፆኦ ልክ ነው፡፡እያንዳንዳችን በቅንጅት የምንሰራቸው በርካታ የልማት ስራዎች አሉብን፡፡
ለውጡ ፍሬ ማፍራት ከጀመረና ህዝቡም ፍሬውን ማጣጣም ከጀመረበት ካላፉት አራት ዓመታት አንስቶ የማይታመን ግን ደግሞ መሰረታዊና ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ወጣቱ፣ጎልማሳው ፣አዛውንቱ፣ ተማሪው ፣መምህሩ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ወዲህ የሚፈልገውና የሚመኘው ሰላምንና ፍቅርን፣ አንድነትን ፣መተሳሰብንና መከባበርን እንዲሁም በጋራ ተነስቶ አገርን መገንባት ብቻ እንደሆነ ነው።
በመደመር እሳቤ እጅ ለእጅ ተያይዘን አገራችንን መገንባት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ ክንዳችን መፍጠር ይኖርብናል፡፡ይህን ማድረግ የምንችለው ደግሞ በጋራ መደመር ስንችል ነው። በጋራ ተነስተንና እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንወዳት ኢትዮጵያችንን በሁላችንም አሻራ መገንባትና በኢትዮጵያ ምድር አንድነትና ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው።
የሁላችንም ምኞትና ዓላማ ሊሆን የሚችለው በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ በመፍጠር የህዝባችንን ህይወት መቀየር ነውና ህዝብንና ሀገርን ሊበጁ ለሚችሉ ለመልካም ነገሮች ሁሉ መደመር መቻላችን ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ስራ ሊሆን ይገባል ፡፡
#prosperity