ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተደርጓል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተደርጓል

  • Post comments:0 Comments
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተደርጓል
ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በአዲስ አበባ የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና እንደምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክርቤት አፈጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳድሮች እና ሚንስትሮች ተገኝተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በውይይቱ የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ አጠቃላይ ገለፃ መደረጉን ተናግረዋል ።
የሰላም ስምምነቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያስጠበቀና የሀገር ሉዓላዊነትን ያከበረ ነው ብለዋል።
የሰላም ስምምነቱ የባከኑ ጊዚያትን የሚክስና የተጉዱ አካባቢዎችን በመልሶ ግንባታ ለማስተካከል ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ላይ መነሳቱን ገልጸዋል ።
በጦርነቱ የተጉዳችው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የሰላም ስምምነቱ ጥቅሙ የሁሉሞ ነው ብለዋል።
የስምምነቱ አተገባበር ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡

Leave a Reply