You are currently viewing ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል፤

ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል፤

  • Post comments:0 Comments

ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል፤

ህወሃት በስሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደት በኢትዮጵያ ብሔር ብሔርብሔረሰቦችና ህዝቦች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው፡፡አሸባሪው የህወኃት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስሜን እዝ አባላት ላይ የደረሰው ጥቃት እና አገራዊ ክህደት ኢትዮጵያዊያን መቼም አንረሳውም፡፡

የሃገር መከላከያ ሰራዊት ለትግራይ ህዝብ በጉ አድራጎት ስራዎችን በማከናወን ባለውለታ ነው፤ ብዙ ዋጋ ለከፈለ ሰራዊት በአሸባሪው ህወኃት ቡድን የተከፈለው ዋጋ ግን አንገታችንን አስደፍቶናል፡፡

በሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላም ቢሆን በሰራዊቱ ላይ ብዙ ስቃይ እና እንግልት ደርሶባቸዋል፤ ጥቃቱም ኢ-ሰብአዊ እና ትውልድ የማይረሳው የክህደት ወንጀል ነው፡፡ በአሸባሪው ቡድን እንግልት ፣ከበባና ውክቢያ ውስጥ የነበሩ የሰራዊቱ አባላት ለተከታታይ ቀናት ታግተው ለርሃብና ለከፍተኛ ውሃ ጥም አጋልጧቸዋል፡፡

ህወሃት የትግራይ ህዝብ ደጀን የሆነው የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ለማድረስ መሞከሩ ከባእድ ወራሪ የከፋ የከሃዲነትን ጥግ የሚያሳይ ነው።

ከዚህ ቀደም ሰራዊቱ ለመደበኛ ተልዕኮ ሲንቀሳቀስ የክልሉ ህዝብ መንገድ በመዝጋት ጭምር ጥለህን አትሄድም እያሉ የሚጠይቁት የህዝብ አለኝታ ነው። በመሆኑም ከ20 ዓመታት በላይ የትግራይን ክልል ብሎም የኢትዮጵያን ድንበር በመጠበቅ ዋልታና ማገር የሆነውን ሰላም አስከባሪውን የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ጥቁር ቀን በአሸባሪው ህወኃት ቡድን አማካኝነት ከፍተኛ ጥቃት ደረሰበት፡፡

ለትግራይ ህዝብ ደጀን ሆኖ እያገለገለ ባለው ሰራዊት ላይ የተቃጣው ጥቃት ከባእድ ወራሪ የከፋ የከሃዲነትን ጥግ የሚያሳይ ስለመሆኑ ብዙዎች የሚስማሙበት ሃቅ ነው።

#prosperity

ምላሽ ይስጡ