You are currently viewing የሰላም መስፈን ጥቅሙ…

የሰላም መስፈን ጥቅሙ…

  • Post comments:0 Comments

የሰላም መስፈን ጥቅሙ የጋራችን ነው፤ሰላም ማጣታችንም ጉዳቱ ለሁላችንም ነው፡፡ የህግ የበላይነት መከበርና የዴሞክራሲ መጎልበት ለኛ ለዜጎች የሚኖራቸው ጠቀሜታ ቀላል አይደለም፤ በመሆኑም ሰላማችን እንዳይደፈርስ፣ ብዝሃነትን ያከበረ ዴሞክራሲያዊ አብሮነታችን እንዲጎለብት ስንል  አንድነታችን የሚፈታተኑ ሃይሎች የሚፈፀሙትን እኩይ ተግባራት መመከት፣ ማጋለጥና ማክሸፍ ብሎም እንደ ሀገር የጀመርነውን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክረን በመቀጠል የሰላም ዘብ መሆናችን በተግባር ልናሳይ ይገባል፡፡

ዛሬ ላይ ከፊት ለፊታችን ያለውን ዳገትና ኮረብታ በጋራ ሀይላችን ንደን የበለፀገችና ለመጪው ትውልድ ያማረች ሀገር ለማውረስ ያስችለን ዘንድ ነገን በማሰብ ከሴረኞችና ከጥፋት ሀይሎች እሳቤ ተላቀን ለምንወዳት ሀገራችን ሌት ተቀን በመስራት ሀላፊነታችንን እንድንወጣ መስራት ይኖርብናል፡፡

የአሁኑ ትውልድ ቀደምት አባቶቻችን የጣሉበትን ታሪካዊ አደራና አገርን እንደ አገር የማስቀጠል ታላቅ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ሙሉ በሙሉ ፊቱን ወደ ልማት ማዞርና አደራውን ለመወጣት ሌት ተቀን ሊተጋ ይገባዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ