አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሄደ
በአንደኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የተመረጠው የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን የፓርቲው ጉባዔ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው የጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት እቅድ ተዘጋጅቶ ውሳኔዎቹና አቅጣጫዎቹ በፍጥነት መተግበር እንዲጀምሩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ኮሚቴው በተጨማሪም አዲስ የተገነባውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የመረቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችንም በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡