You are currently viewing በአመራርና በአባላት መረጃ ቋት ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ተካሄደ

በአመራርና በአባላት መረጃ ቋት ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments

በአመራርና በአባላት መረጃ ቋት ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ተካሄደ

በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ የተዘጋጀው የአመራርና የአባላት መረጃ ቋትን በተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና በአዳማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሊድ አልዋን ይህ ግምገማዊ ስልጠና ባለፉት ጊዚያት የነበሩ ጠንካራ ጎኖቻችንን በማስቀጠልና ድክመቶቻችንን ለይተን በቀጣይ እንዳይደገሙ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም በ2013 ዓ/ም በአመራርና አባላት መረጃ ቋት ሲዳማ፣ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም ማሳየታቸውን ጠቀሰው እስካሁን ባለው ሁኔታ የመረጃ ቋት አፈጻጸም 90% መድረሱን ተናግረው መረጃዎችን ከመሰብሰብ ባሻገር ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ግምገማዊ ስልጠና አስራ አንደኛ ክልል ሆኖ በአዲስ የተዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ጨምሮ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምላሽ ይስጡ