የአሸባሪው ትህነግ ዛሬም…

የአሸባሪው ትህነግ ዛሬም…

  • Post comments:0 Comments
የአሸባሪው ትህነግ ዛሬም ድረስ ማብቂያ የሌላቸው የውሸት ትርክቶች የቱንም ያህል አደባባዮችን የሞሉ ቢመስሉም በስተመጨረሻው የቡድኑ ርካሽ ባህሪ መገለጫ ከመሆን ባለፈ በራሳቸው ቆመው ለመሄድም ሆነ ረጅም መንገድ ለመጓዝ አቅም እንደሌላቸው በተጨባጭ እየታየ መጥቷል፡፡
 
ትህነግ ዛሬም እንደኮሶ ከተጣባው አመሉ አልተላቀቀም፡፡በእርግጥም ይላቀቃል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ይህ የሽብር ቡድን ዛሬም ዋነኛ ስልቱ ሐሰተኛ መረጃ በመፈብረክና በማሰራጨት ሆኗል፡፡
 
በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣በአማራና በአፋር ልዩ ሃይሎችና ህዝባዊ ሚሊሻዎች እየደረሰበት ያለውን ውርጅብኝ መቋቋም ተስኖት ወደ መጣበት አግሬ አውጪኝ ማለት ሲጀምር የሽብር ቡድኑ መሪዎች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ በማለት የትግራይ ሰራዊት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በራሱ ፈቃድ ለቆ ወጧል ይላሉ፡፡
 
በወገን ሃይል ድባቅ እየተመታ የሚይዘው የሚጨብጠው ያጣው የጠላት ሃይል አይደለም በራሱ ፈቃድ ሊመለስ ይቅርና ሞክሮት ባይሳካለት እንጂ የአራት ኪሎን ስልጣን ዳግም በእጁ ባስገባ ነበር፡፡
 
አሁን እየተገኘ ላለው ስኬት አንዱ ማሳያ ደግሞ መላው ኢትዮጵያዊያን ለሰራዊታችን እያሳዩት ያለው ጠንካራ ደጀንነት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ኢትዮጵያውያን ከመቼም ጊዜ በላይ አንድ ሆነው ተነስተዋል፡፡
 
ትህነግ አንድ እንዳይሆን ሴራ ሲሸርብበት የነበረው ህዝብ ዛሬ አንድ ሆኖ ጠላትን ድባቅ እየመታ መፈጠሩን እንዲጠላው እያደረገው ነው፡፡ከጥንት ጀምሮ በሀገራቸው ጉዳይ የማይደራደሩት ኢትዮጵያውያን አገር ሊያፈርሱ የመጡ ጠላቶቻቸው ወኔና ብርታት ሆኗቸው ስለአገራቸው አንድ ላይ ቆመዋል፡፡
 
ዛሬ ላይ ከዳር እስከ ዳር እየተነቃነቀ ያለውን ኢትዮጵያዊነት ለተመለከተ የአሸባሪው ትህነግ ዕድሜ እያጠረ መምጣቱን ያሳያል፡፡

Leave a Reply