ኢትዮጵያ የጀመረችው የለውጥ ጉዞ ብዙም ሰላም ያልሰጣቸው አገራት፤ከአሸባሪው ህወኃት የጥፋት መንገድን ጋር ተቆራኝተዋል። በመደገፍም የአገሪቱን ሠላምና መረጋጋት፤ ከዛም ባለፈ ሕልውናዋን ስጋት ውስጥ በሚጨምር የተናበበ የጥፋት ዘመቻ ውስጥ ይገኛሉ።
አሜሪካ የአገር ነቀርሳ የሆነውን የአሸባሪው ህወኃት ተፈጥሯዊ ሞት ለመቀልበስ በብዙ መልኩ ከቡድኑ ጋር ሰልፈኛ ሆናለች። የቡድኑን የሽብር ተግባሮች እንዳላየ ከማየት ጀምሮ በመንግሥት ላይ ያልተገቡ ጫናዎችና ማስፈራሪያዎች እስከ ማሰማት ድረስ የሚደርሱ ተግባራትን ታከናውናለች።
መንግሥት ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን በአሸባሪው ቡድን ላይ ሲወስድ ከፍ ባሉ ጩኸቶች ዓለም አቀፍ መድረኮችን ማጣበብ፤ ቡድኑ ስኬታማ የሆነ ሲመስላት ደግሞ ዝምታን በመምረጥ ግልጽ የሆነ ድጋፏን ለአሸባሪው ቡድን በመስጠት ከአሸባሪው ቡድን ጋር ብቻ ሳይሆን ከቡድኑ የሽብር ተግባር ጋር ያላትን አጋርነት ታሳያለች።
አሁን ያለው የሕዝቡ ፈተና እና ትግል በታሪኩ ተሻግሮ ከመጣቸው የሚያንስ እንጂ የሚበልጥ ባለመሆኑ አሸናፊነቱ አያጠያይቅም።