You are currently viewing እንደ አገር የተቃጣብንን ጥቃት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው መቀልበስ ችለዋል- አቶ ላክዳር ላክባክ 

እንደ አገር የተቃጣብንን ጥቃት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው መቀልበስ ችለዋል- አቶ ላክዳር ላክባክ 

  • Post comments:0 Comments

እንደ አገር የተቃጣብንን ጥቃት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው መቀልበስ ችለዋል- አቶ ላክዳር ላክባክ

በአሸባሪው ህወኃት እንደ አገር የተቃጣብንን ጥቃትና እየደረሰብን ያለውን ፈተና ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው መቀልበስ መቻላቸውን የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ላክዳር ላክባክ ገለጹ፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊው በሰጡት መግለጫ በጠ/ሚ ዐቢይ የተመራው ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት እንደ አገር የገጠመንን ፈተና መቀልበስና ለድል መብቃታችን ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ የሚጠብቅና የአባቶቹን አደራ የሚወጣ ትውልድ ዛሬም እንዳለ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ሰራዊታችን በጠላት ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ላክዳር ለሰራዊታችን እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ወጣቶች የአገር መከላከያ ሰራዊትን በስፋት ተቀላቅለው አገራቸውን ከጠላት መጠበቅ ይኖርባቸዋል ያሉ ሲሆን መላው ኢትዮጵያዊያን አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ጀምሮ በአስራ አንዱም ግንባሮች ተሰልፈው ደጀንነታችንን አጠንክረው እንዲቀጥሉና በተግባር እንዲያሳዩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ