ከአባቶቻችን የወረስናትን አገር ከጠላት ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን-የድሬዳዋ ወጣቶች

ከአባቶቻችን የወረስናትን አገር ከጠላት ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን-የድሬዳዋ ወጣቶች

  • Post comments:0 Comments
ከአባቶቻችን የወረስናትን አገር ከጠላት ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን-የድሬዳዋ ወጣቶች
*********************************************************************
አገር ለማፍረስ እኩይ ተልዕኮ ያነገበው ጠላት በሁሉም አካባቢዎች ሰላም እንዳይኖር ስለሚፈልግ ወጣቶች አካባቢያቸውን ነቅተው መጠበቅ አለባቸው ሲል ወጣት ሰብስቤ ታደሰ ተናገረ፡፡
ጠላት በሁሉም አካባቢ ሽብር መፍጠር ስለሚፈለልግ ወጣቶች አካባቢያቸውን ነቅተው መጠበቅ አለባቸው ያለው ወጣት ሰብስቤ ከአባቶቻችን የወረስናትን አገር ከጠላት ጠብቀን ለትውልድ ማስተላለፍ ግዴታችን ነው ብሏል፡፡
የ05 ቀበሌ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ የሆነችው ወጣት ህይወት ጌታቸው በበኩሏ ሴቶች ለአካባቢያቸው ሰላም ጉልህ ሚና እንደመኖራቸው መጠን ሁሌም በተጠንቀቅ አካባቢያቸውን መቃኘት ይኖርባቸዋል ስትል ተናግራለች፡፡
የገጠመንን አገር የሚያፈርስ ጠላት በአንድ ግንባር ብቻ ማሸነፍ ስለማይቻል ወጣቶች መንግስት ባወጣቸው አስራ አንድ ግንባሮች ተሰማርተው ሊሳተፉ ይገባል ያለችው ወጣት ፍሬያሬድ ደሳለኝ አካባቢን በመጠበቅ ግንባር መሰለፏን ተናግራለች፡፡
ወጣት ፍሬያሬድ አያይዛ እንደገለጸችው ምሽት ላይ አካባቢዋን እየጠበቀች ባለችበት ወቅት ባደረገችው ፍተሻ በማዳበሪያ ውስጥ ከጫት ጋር የታሰረ ሁለት ሚሊዬን አካባቢ የሚደርስ ብር መያዟንና ለአካባቢው ፖሊስ ማስረከቧን ተናግራለች፡፡
በድሬዳዋ ከተማ መንደር አንድ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ኦፊሰር የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር አብዲ ሃምዛ ወጣቶች አካባቢያቸውን ተደራጅተው በመጠበቃቸው ምክንያት ቤት ሰብሮ ስርቆት፣ቂሚያና ሌሎች የወንጀል ስራዎች መቀነሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢንፔክተሩ አያይዘውም ወጣቶች ባደረጉት ፍተሻ ሁለት ሚሊዬን ብር በማዳበሪያ ውስጥ ታስሮ ማግኘታቸውን ገልጸው ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጣቢያ መላኩን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply