ለአንተ ነው የመጣሁት እያለ በህልውናህ የመጣ ጠላት
በአብዲ ኬ
*********************************************************************
ለአንተ ለመድረስ ነው የመጣሁት እያለ በህልውናህ የሚመጣው እኩይ ቡድን ሁለት ጊዜ እንዳያታልልህ መንቃት ግድ ይላል።
አሸባሪው ህወሃት በአፉ የሚናገረውና ተግባሩ ሁሌም ለየቅል ነው። ሲናገር ለህዝብ፣ በተግባር ግን ፀረ ህዝብ ቡድን መሆኑ ግልፅ ነው። የትግራይን ህዝብም፤ ነፃ አውጭህ ነኝ፣ የመብትህ ጠበቃ ነኝ ገለመሌ እያለ በአፉ እየደለለ እንደ ቁስ መጠቀሚያ አድርጎታል።
ከአምስት አስርት አመታት በፊት ነፃ ላወጣህ ነው ብሎ ተነስቶ ህዝቡን በእሳት ማግዶ ወደ ስልጣን መጣ፣ ከመጣ ጀምሮ ህይወቱን ለገበረለት ድሃ ህዝብ ምንም የረባ ነገር ሳይሰራ በስሙ ሲዘርፍና ለጥቂቶች ሃብት ሲያካብት ኖረ።
ዘራፊነቱና እኩይ ተግባሩ ታውቆበት ከስልጣን ሲወገድም፤በስልጣን ዘመኑ የረባ መሰረተ ልማት እንኳን ያልዘረጋለት፤ እነርሱ ሲንደላቀቁ ሲራብ ሲጠማ የኖረ ህዝብ ጉያ ሂዶ ተወሸቀ። ህዝቡ ጥያቄ እንዳያነሳበትም ተከበሃል፣ ህልውናህ አደጋ ውስጥ ነው በሚል የውሸት ትርክት ዳግም ህዝቡን አታሎ እናት አገሩን እንዲወጋ ለጦርነት አዘጋጀው። ለእልቅት፣ ለረሃብና መከራም ዳረገው።
ይህ እኩይ ቡድን አማራንና ሌሎች ህዝቦችንም ለማታለል፣ ከዛሬ 30 አመት በፊት የተጠቀመውን ማታለያ ዳግም መጠቀም ይፈልጋል። አኛ ከአብይ ጋር እንጂ ከእናንተ ጋር ምን ችግር የለብንም ይላል፣ የዛሬ 30 አመትም ከደርግ እንጂ ከእናንተ ጋር ፀብ የለኝም ብሎ በህዝቡ ተደግፎ ወደ ስልጣን መጣ፤ ከመጣ በኃላ ግን ያ በህዝብ ድጋፍ ወደ ስልጣን ያመጣውን ህዝብ እንደ ታሪካዊ ጠላት ፈርጆ ፈርጀ ብዙ ጉዳት ሲያደርስበት ኖረ።
ዛሬም ደግሞ «ከእናንተ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለኝ» ብሎ በይፋ ዝቶ ወጣቶችን አጋድሞ እያረደ፣ ሴቶችን እየደፈረ፣ እያወረደ፤ ሃብት ንብረት እየዘረፈ፤ መውሰድ ያልቻለውን እያወደመ፣ ህዝቡ ወጥሮ ሲመክተው እኔ ከአብይ እንጂ ከናንተ ችግር የለብኝም ይላል።
ደግነቱ ግን ለአንተ ነው የመጣሁት እያለ በህልውናው የመጣበት ጠላት መሆኑን የተገነዘበ የአማራና የአፋር ህዝብ እንደ ትግራይ ህዝብ ሁለቴ የሚታለልለት አልሆነም፤ ይህ ቡድን ሰርጎ በገባበት ሁሉ የእግር እሳት ሆኖ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶታል።
በአውደ ውጊያ ሁሉ ከአገር መከላከያና ልዩ ሃይል ጋር አብሮ ተሰልፎ ይህን ዘላለማዊ ጠላቴን ሳልቀብር አልመለስም እያለ ይገኛል። በድል ግስጋሴውም ቀጥሎበታል።