ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ታሪካችን ሁሉ የአሸናፊነት ነው – አቶ መለሰ አለሙ

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ታሪካችን ሁሉ የአሸናፊነት ነው – አቶ መለሰ አለሙ
 
ከየካ ክፍለ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች አሸኛኘት ተደርጓል፡፡
“እኔ እያለሁ ኢትዮጵያን አሳልፌ አልሰጥም!!” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች አሸኛኘትና የአከባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ ለማስጠበቅ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ህዝባዊ ሰራዊት የምረቃ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሌሎች አገሮች የተተገበረን አገር የማፍረስ ሴራ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ነፃነታችንን አስጠብቀን እንቀጥላለን ፤ ይህንን በመገንዘብም መላው የመዲናዋ ነዋሪ እየሰጠ ያለውን ዘርፈብዙ ምላሽ የሚደነቅ እንደሆነ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ታሪካችን ሁሉ የአሸናፊነት ነው ያሉት ሃላፊው ÷ አገራችን በኛ ዘመንም ክብሯና ነፃነቷ ተጠብቆ ትቀጥላለች ብለዋል አቶ መለሰ አለሙ፡፡
የአሸባሪው ህውሓት የሀሰት ወሬና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በኢትዮጵያ ቦታ የለውም ፤ የኢትዮጵያውያን አቅም እውነት እና እውነት ብቻ በመሆኑ ድላችን ቅርብ ነው ብለዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው ÷ አዲስ አባባን ጨምሮ በመላው ሃገሪቱ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሰራዊቱን በማጀገን እና በመደገፍ እየተከናወኑ ባሉት ተግባራት በመከላከያ ሰራዊት ስም አመስግነዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ይታያል ደጀኔ ÷ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት ከመጠበቅ ባለፈ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከ55 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማድረጉን መግለጻቸውን ከከተማው ፕረስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምላሽ ይስጡ