You are currently viewing በሀረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች ምርጫና ህዝበ ውሳኔ በሰላም እየተካሄደ ነው፡- ብርቱካን ሚዴቅሳ

በሀረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች ምርጫና ህዝበ ውሳኔ በሰላም እየተካሄደ ነው፡- ብርቱካን ሚዴቅሳ

  • Post comments:0 Comments
በሀረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች ምርጫና ህዝበ ውሳኔ በሰላም እየተካሄደ ነው፡- ብርቱካን ሚዴቅሳ
በሀረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች እየተካሄደ ያለው ምርጫና ህዝበ ውሳኔ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ገለጹ፡፡
ሰኔ 14 የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ከሰላም እና ደህንነት አንፃር ሊካሄድባቸው ባልቻሉ ክልሎች የምርጫ ሂደቱ ዛሬ ጀምሯል፡፡
ከማለዳ አንስቶ እየተካሄደ ያለው ምርጫም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየሄደ እንደሆነ ምርጫ ቦርድ አብራርቷል፡፡
ከሰላምና ፀጥታ አንፃር በሶማሌ ክልል ሞያሌ የምርጫ ጣቢያ ላይ አስፈፃሚዎች ባቀረቡት የፀጥታ ስጋት ምርጫው እንዳይካሄድ ከመደረጉ ውጭ የጎላ ችግር አልገጠመም ብለዋል የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ፡፡
በደቡብ ክልል የህዝበ ውሳኔ በሚደረግባቸው እንዲሁም ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ሰላማዊ ሂደት እንዳለ ገልጸዋል፡፡
በጉረፈርዳ አካባቢ በነበረው የፀጥታ ችግር የመራጮች ምዝገባ በሚገባው ልክ ባለመካሄዱ ችግሩን ለመፍታት በዛሬው እለት መራጮች እየተመዘገቡ ድምፅ እንዲሰጡ እየተደረገ ነው ብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡
ምርጫውንና ህዝበውሳኔውን ሙሉ በሙሉ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች እየተዘቡት እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ምላሽ ይስጡ