በመድረኩ የተገኙት የክልሉ በም/ል ርዕስ መሰተዳድር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሴ አዳም ስሆን የ2013 ጠቅላላ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና የ2014 ዕቅድ ኦሬንቴሽን ላይ ከሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ከተወጣጡ የብልፅግና ፅ/ኃለፊዎች ፣ የሊጎች አመራሮች እና የዞኖችና የወረዳዎች አስተዳደሮች ጋር ሰፊው ውይይት ተካሄዷል። በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርቱ የ2013 የሥራ አፈፃፀም ምን ይመሰል እንደ ነበር ፣ ድክመቶች እና ጣንካራ ጎኑን ጎልቶ በሚያሳይ መልኩ የቀረበ ስሆን ተሰብሳቢዎች በቀረበው የ2013 የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት በመካሄድ በአፈፃፀም ላይ የታዩ ጥንካሬ እንደ ጥንካሬ የሚወሰድ መሆኑን በማግባባት ግን ከታዩት ከውስን ድክመቶች ትምህርት በመውሰድ በቀጣይ መሻሻል እንደ አለበት አስቀምጧል። የ2013 የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በኋላ የ2014 ዕቅድ ላይ በተመሣሣይ መልኩ ሰፊው ውይይት እና ግምገማ በመካሄድ የቀረበው የ2014 ዕቅድ ኦሬንቴሽን በሙሉ ድምፅ ያፀደቁት ስሆን በመጨረሻም በመድረኩ የክልሉ ርዕስ መሰተዳድር አቶ አወል አርባ የተገኙ ስሆን የ2013 የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩት ዞኖች እና ወረዳዎች ኮምፒውተሮች ፣ ላፕቶፖች ፣ ዋንጫዎች እና የምስጋና ወርቀቶች ተሰጧል። የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ይህ ሽልማት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩት ዞኖች እና ወረዳዎች ብቻ ሳይሆን ሳይሸለሙ ለቀሩት ዞኖችና ወረዳዎች ጭምር በመሆኑ ሌሎች ከተሸላሚዎቹ በመማርና ትምህርት በመውሰድ ለ2014 ዕቅድ አፈፃፀምና ከወዲሁ ለፓርቲው ሥራ መዘጋጀት እንደሚገባ ገልጿል ። በተጨማሪ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተካሄደ ስሆን ለሚልሺያ ፣ ለልዩ ኃይል እና ለመከላከያ ምልመላ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ልዩ ትኩረት መስጠት አንደሚገባ በመግለፅ ለሁሉም ወረዳዎች የመከላከያ ምልመላ ኮታ በመሰጠት ከወዲሁ ለዚህ ሥራ ዛሬና ነገ ሳይባል በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላው አጠናቀው ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። በመጨረሻም የክልሉ በም/ል ርዕስ መሰተዳድር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሴ አዳም የ2014 ዕቅድ ከሁሉም ዞኖች የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር የስምምነት ሰነድ በመፈራረም በቀጣይ ከዚህ ስምምነት ሰነድ በመነሳት ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ ገልጿል።
