You are currently viewing በወቅታዊ የአገራዊ ሁኔታን በማስመልከት ከልዩ ልዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

በወቅታዊ የአገራዊ ሁኔታን በማስመልከት ከልዩ ልዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
በወቅታዊ የአገራዊ ሁኔታን በማስመልከት ከልዩ ልዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተካሄደ
ከልዩ ልዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ የፓርቲ መሪዎች በወቅታዊ የአገራዊ ሁኔታ ዙሪያ በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
መድረኩን የመሩት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የዘርፍ አስተባባሪ ሚኒስትርና የስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል ክቡር አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ይህ የውይይት መድረክ አገርን ከጥቃት ለማዳን እና በአገራዊ ጉዳይ ላይ ሁሌም በጋራ መስራትና በአንድ ላይ መቆም በማስፈለጉ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡
ከፊት አሸባሪው የህወኃት ቡድን ይሰለፍ እንጂ በርካታ ሃይሎች እጃቸው አለበት ያሉት አቶ ተስፋዬ ኢትዮጵያን ለመበታተን ከውስጥም ከውጭም ያሉ ሃይሎች በጥምረት እየሰሩ በመሆናቸው ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችንን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የተከፈተብን ጥቃት በግንባር ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ፣በሃሰት ፕሮፖጋንዳና በልዩ ልዩ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላት ፎርሞች የኢትዮጵያን ክብርና ዝና የማጠልሸት ስራ በመሆኑ ይህንን ለመቀልበስ የሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ንቁ ተሳትፎ ያስፈልጋል ተብሏል፤
ለውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በሚንስትር ማእረግ የምርጫና የዲሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዛዲግ አብርሃ በሰሜን በኩል የተከፈተው ጦርነት ከኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ውጭ የስርዓት ለውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰው የኢኮኖሚ አሻጥር እንዲፈጠር በማድረግ ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ እንዲማረር በማድረግ መንግስት ላይ ለማነሳሳት እየሰሩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡
ስለ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ውይይት ለማድረግ በአጭር ጊዜ ጥሪ ተደርጎላቸው ከተለያዩ ቦታዎች ለተገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ያላቸውን ምስጋና ያቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሔል ባፌ ወቅቱን በአግባቡ ከተጠቀመንበት እንደ አባቶቻችን አኩሪ ታሪክ የምናስመዘግብበት መሆኑን በመረዳት ሁላችንም አሸባሪውን የህወኃት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት ማገዝና መደገፍ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ