You are currently viewing የህወሓት ቡድንና መሰሎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል- የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች

የህወሓት ቡድንና መሰሎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል- የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች

  • Post comments:0 Comments
የህወሓት ቡድንና መሰሎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል- የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች
የህወሓት ቡድንና መሰሎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ።
ዛሬ የመከላከያ ሠራዊትን በሚደግፍ ፣ የህወሓት ቡድንና መሠሎቹን በሚቃወመው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ለሀገራቸው የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ የህወሓት መቀበሪያ እለት ነው ሲሉ የገለፁት ነዋሪዎችም የሽብርተኛው ቡድን ሴራና የክፋት ተግባር አብቅቶለታልም ነው ያሉት
የትግራይ ህዝብ ወገናችን ነው ጁንታው ጠላታችን ነው ብለዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ በአሁኑ ሰዓት በሀዋሳ አለም አቀፍ እስታዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ምላሽ ይስጡ