You are currently viewing የአሸባሪው ትህነግ እና የኦነግ ሸኔን ትንኮሳ በመቃወም በዱከም ከተማ ሰልፍ ተካሄደ

የአሸባሪው ትህነግ እና የኦነግ ሸኔን ትንኮሳ በመቃወም በዱከም ከተማ ሰልፍ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
የአሸባሪው ትህነግ እና የኦነግ ሸኔን ትንኮሳ በመቃወም በዱከም ከተማ ሰልፍ ተካሄደ
 
የአሸባሪውን ትህነግ እና የኦነግ ሸኔን ትንኮሳ በመቃወም በዱከም ከተማ ሰልፍ ተካሄደ።
የትህነግን ትንኮሳ ለመመከት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም እንደሚታገሉ በዱከም ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
በሰልፉ ላይ ከዱከም ከተማ እና ከአካባቢው የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በሰልፉ “አሸባሪው ሸኔና ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች ናቸው፣ “በውድ መስዋዕትነት የተጎናፀፍነውን ነፃነት በመስዋዕትነታችን እንጠብቃለን፣ “ወያኔን ባስወገድነው የተባበረ ክንዳችን ሸኔን እንነቅላለን፣ “ሸኔ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ወያኔ ነው፣ “ሸኔና ወያኔ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችና ቅጥረኞች ናቸው “እና” የኢትዮጵያ ብልፅግና በውስጥና በውጭ ጠላቶች አይደናቀፍም” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ ተሾመ ግርማ፥ ህዝቡ የሸኔን እና የወያኔን ጥምረት በመቃወም እና ሠላሙን ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኛ አቋም በማሳየቱ አመስግነዋል።
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረገውን የአሸባሪ ቡድኖች አካሄድ ማክሸፍ የሚቻለው እንደ አሁኑ ሁሉም በጋራ ሲሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
“ከወደቁ በኋላ ለመነሳት መፍጨርጨር ለመላላጥ” በመሆኑ ይህ የጥፋት ቡድን ከእነእኩይ ስራው በወደቀበት ተቀብሮ እንዲቀር ህዝቡ በጀመረው አግባብ የበኩሉን እንዲወጣ ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።

ምላሽ ይስጡ