በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመምከር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ወጣቶች ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
የአቋም መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
የወጣት አደረጃጀቶች ባመቻቹት በዚህ መድረክ እኛ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣን ወጣቶች በወቅታዊ የሃገራችን ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገናል፡፡ በመድረካችን ላይም አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያ ሃገራችንን ለመበታተን እና ክብርዋን ዝቅ ለማድረግ በአፉ በከፍተኛ አመራሮቹ ከሚለውና ከሚፎክረው ባሻገር በተግባር ግልፅ ወረራ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፋራረስ ከሌሎች የውስጥም የውጭም አካላት ጋር እየሰራ ያለውን ጥፋት በሚገባ ተገንዝበናል፡፡ መንግስታችንም በተደጋጋሚ በህወሃት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ህወሃትን ሲደገፍ በነበረው የትግራይ ህዝብ ሲባል እየተከተለ ያለውን የሰላም መንገዶች መገንዘብ ችለናል፡፡ ይህ አሸባሪ ሃይል የፈጠረውን አደጋ እና ከኛ ከወጣቶች ወቅቱን በመረዳት መያዝ ያለብንን አቋሞች በዝርዝር ተወያይተን ከታች የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫዎች አውጥተናል፡፡
1. አሸባሪው ህወሃት የፌደራል መንግስት ያወጣውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በግልፅ በአማራ ክልል እና አፋር አከባቢዎች የፈፀመውን ወረራ እና ግልፅ ጦርነት እናወግዛለን፡፡ በዚህ ወረራው በመቶ ሺዎች አፈናቅሎል፣ በደረሰበት ሁሉ ሃብት ንብረት ዘርፏል ፍፁም ከኢትዮጵያዊነት በወጣ ስሜት በአፋር ክልል ከ240 በላይ ንፁሃንን ከዚህ ውስጥ ከ140 በላይ ምንም የማያውቁ ህፃናትን በሸሹበት የጤና ተቋሞም ላይ በመድረስ ከባድ መሳርያንም በመጠቀም ጭምር ያደረሰውን ጅምላ ጭፍጫፋ አምርረን እናወግዛለን! የአፋር ብሄራዊ ክልልም ይህንን ተከትሎ ያወጣውን የሃዘን መግለጫ እኛ ወጣቶች የተሰማንን ሃዘን እየገለፅን በሁልም መልኩም ከክልሉ መንግስት ጎኑ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
2. አሸባሪው ህወሃት በሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የተነሳ በየደረሰበት አውደ ውግያ ሁሉ የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል የሆነውን ህፃናትን በጦርነት ማሳተፍ ህግ በመጣስ ህፃናትን በሃሸሽ አደንዝዞ እና አዲስ አበባን ልንቆጣጠር ነው በሚል ፕሮፖጋንዳው ህፃናትን በጦርነቱ እየማገደ መሆኑን ታዝበናል፡፡ በዚህ በተሳሳተው የአሸባሪው ውሸት ለሚማገዱ ህፃናት ከልባችን እያዘንን ይህንን የአሸባሪውን ቡድን ተግባር በፅኑ እንቃወማለን፡፡ የትግራይ ወጣቶችም ከዚህ አሸባሪ ቡድን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተላቀው ከኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጋር በጋራ ቆመው አገራቸውን እንዲታደጉ ጥሪ እናቀርባልን፡፡
3. አሸባሪው ህወሃት በጦር ግንባር ብቻ ሳይሆን በከፈተብን የዲፕሎማሲ እና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አለም አቀፍ ማህበረሰቡ የተዛባ አመለካከት እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ እና ስልጣን ላይ በነበሩበት ሰዓት ብሄራዊ ጥቅማችንን ወደ ጎን በመተው በፈጠሩት ያልተገባ ግንኙነት መጠቀምያ በማድረግ አለም አቀፍ ማህበረሰቡን የተዛባ መረጃ በመስጠት ዓለምን በተዛባ አቋም ውስጥ መክተቱትን ታዝበናል፡፡ እኛ ወጣቶች ይህንን በተዛባ መልኩ የተቀረፀ ዐለም አቀፍ ማህበረሰብ እውነታውን በመረዳት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲሰለፍ እየጠየቅን ሁላችንም ወጣቶችም የኢትዮጵያ አምባሳር በመሆን በሁሉም መንገድ ስለ ሃገራችን እውነታውን ለማሳዎቅ ቆርጠን የተነሳን ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ግንባሩም ላይ ወጣቶች በስፋት በመሳተፍ አገራችንን ለመታደግ እና የኢትዮጵያን እውነት ለአለም ለማሳወቅ ቆርጠን የተነሳን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4. እኛ ወጣቶች ኢትዮጵያን ለማዳን የትም፣ መቼም በምንም ለመዝመት ወስነናል፡፡ የተቃጣብንን ወራራም ለመቀልበስ እኛ የኢትዬጵያ ወጣቶች፣ የሃገር መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል ዘብ ለመቆም ወስነናል፡፡ በግንባር ከመሰለፍ ባሻገር በየአከባብያችን ለየ ከተሞቻችንን ዘብ በመቆም የራሳችንን ሰላም በማስጠበቅ አከባብያችንንም ከሰርጎ ገብ ለመጠበቅ ቆርጠን ተነስተናል፡፡ ለሃገር መከላከያ ሰራዊታችንም የሚገባውን ክብር በመስጠት ምን ግዜም በሁሉም መልኩ ከጎኑ እንቆማልን፡፡
5. በተለያየ ዓለም ሃገራት የምትገኙ የኢትዬጵያ ወዳጆች እና አገራት ሆይ ኢትዬጵያ እንደዚህ ቀደሙ የተጋረጠባትን የተቀናጀ የውስጥ እና የውጭ ጠላት እና ባንዳ ድባቅ መትታ በድል ከዓለም ፊት ከፍ ብላ የምትታይበት ግዜ ቅርብ ነው፡፡ ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ በተለይም ምዕራባውያንና በነሱ አስትንፋስ የምተነፍሱ ሃገራትና ሚዲያዎች ሆይ ኢትዮጵያውያንን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በዝምታ ማለፉን አስተዛዝቦናል፡፡ በማይካድራ አሸባሪው ህወሃት ያሰማራቸው ሳምሪ የተባሉ ወጣቶች አማካኝነት አማራ ወንድሞቻችን ተለይተው በጅምላ ሲጨፈጨፉ ዝም ማለታችሁ አሰተዛዝቦናል፣ አሁን በቅርብ ከተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ በሆላ አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክል እና አፋር ክልል ያደረገውን ወረራ እና እሱ ሌሎች እንደሚለው ሳይሆን ራሱ ቀድሞ የተለከፈበትን የተስፋፊነት አባዜ አይታችሁ እንዳላያችሁ ማለፋችሁ አስተዛዝቦናል፣ከተኩስ አቁም በፊት አለም አቀፍ ሚዲያዎቻችሁን ተጠቅማችሁ የአማራ ልዩ ሃይል እና የኤርትራ ሳራዊትን በማየገባችሁ ገብታችሁ ከትግራይ ውጡ ያለው አፋችሁ ምነው አሁን አማራ ክልል እና አፋር ክልል ላይ ያለውን አሸባሪ ቡድን ውጣ ለማት አፋችሁ ተያዘ፣ አፋር ላይ አሸባሪው ቡድን ያደረሰውን ጅምላ ጭፍጨፋ ምነው ለማውገዝ ተናነቃችሁ፣ የአማራ የአፋር ሴቶች መደፈር መጎሳቆል መንገላታት አልታያችሁ አለም አለም አቀፍ ማህበረሰቡ እና የታዛባችሁ ምእራብያውያንና ሚዲያዎች ሆይ ይ ቀን ያልፋል የኢትዬጵያ ወጣቶች በተግባራችሁ አፍረናል፡፡ ገብቶ ቡድን አሸባሪውኢትዬጵያም ለቅኝ ገዥ የማትመቸ ቅኝ እገዛለሁ ብሎ የሚመጣን አካልም ሁለት ሶስቴ አንበርክከን እንደላክነው ታሪካችንን በሚገባ ታውቁታላችሁ፡፡ አሁንም እንላለን ኢትዬጵያ ልዑላዊት ሃገር ነች እኛ ወጣቶችዋም ይህችን ታፍራና ተከብራ የኖረች አገር ክብርዋ ዝቅእንዳይል ሁሉንም መስዋትነት ለመክፈል ከፊት ተሰልፈናል፡፡ ይህንን እውነታ አውቃችሁ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መልክ ያለውን እንቅስቃሴአ እና አላስፈላጊ የእጅ ጥምዛዛ በመተው የረሳችንን ጉዳይ በራሳችን እንድንፈታው እጃችሁን ከሃገራችን ላይ እንድታነሱ እንላለን፡፡
6. እኛ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጠባችን ከትግራይ ወጣትና ከትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም፡፡ ጠባችን ለወጣቶች የማትመች አገር፣ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ከማይፈልገው አሸባሪ ጋር ነው፡፡ ጠባችን በነፃነት እንድንደራጅ፣ ሃሳባችንን እንዳንገልጽ፣ በነፃነት ቀና ብለን እንዳንሄድ እያደረገ ካለው አሸባሪ ቡድን ጋር ነው፡፡ የእኛ ጠብ ከዚህ ራስ ወዳድ ተስፋፊና አገር ለማፍረስ ሲዖል ደርሼም ቢሆን እመለሳለሁ ብሎ ከሚያስበው ቡድን ጋር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አሁንም እንጠይቃችኋለን ይህ አሸባሪ ቡድን ለእናንተም አይጠቅምም እንደማይጠቅምም አይታችሁታል፡፡ ይልቁንስ ከእኛ ከወንድሞቻችሁ ጋር ሊነጥላችሁ እየሞከረ ነው፡፡ በመጨረሻም ለመላው የትግራይ ወጣቶች ኢትዮጵያን በጋራ እንድንታደጋት ጥሪ እናቀርባን፡፡
ኢትዬጵያ በልጆችዋ ጥረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
ክብር በተለያየ ግንባር ተሰልፈው ህይወታቸውን ለሰው ለሰማዕታት ኢትዮጵያውን ሁሉ!
ነሃሴ 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ!