በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ወንዶ ክላስተር ስር የሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአለታ ወንዶ ከተማ “ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን እንሆናለን” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ወንዶ ክላስተር ስር የሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአለታ ወንዶ ከተማ “ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን እንሆናለን” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ወንዶ ክላስተር ስር የሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአለታ ወንዶ ከተማ “ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን እንሆናለን” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
 
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ወንዶ ክላስተር ስር የሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በጋራ በአለታ ወንዶ ከተማ “ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን እንሆናለን” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን በድጋፍ ሰልፉ ላይም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አቶ አበዙ አሰፋዉ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ከስድስቱም ወረዳዎች እና ከአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አመራሮች በተገኙበት የድጋፍ ሰልፉ ተካሂዷል ።
 
በድጋፍ ሰልፋ ላይ በመገኘት ለሰልፋ ታዳሚዎች መልዕክት ያስተላለፋት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት የሚካሄደዉ ይህ የደጀንነት ሰልፍ የሀገር አለኝታ የሆነውን ጀግናዉን መከላከያ ሰራዊታችንን ለመደገፍ እና ከጎኑ ነን ብላችሁ በመውጣታችሁ በራሳቸዉና በክልሉ መንግስት ስም በማመስገን የሀገራችንን ብልፅግና ወደ ኃላ ለመጎተት በሴረኞቹ የ ጁንታውና እና በተላላኪዎቹ እየተመራ የሚገኘው ሀገርን የማፈራረስ ዕቅድ እንዳይሳካ ሁሉም የሲዳማ አካባቢ መቃውሙን የዛሬው ሰልፍ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ኃላፊው አክለውም የኢትዮጵያ ሰላም ሲደፈርስ ዝምታን ያልመረጡ የክልሉ የቀድሞ ጀግኖች ዛሬም የሀገርን ዳር ድንበር ለመጠበቅ እየተዋደቀ ከሚገኘው መከላከያ ሰራዊታችን ጋር እንዲሰለፉ አሳስበው በመጨረሻም ህዝቡ በመረጠው መንግስት እንዲተዳደር የአለም መንግስታት ከጫናቸው እንዲታቀቡ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
 
የአለታ ወንዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌደሁን ጋቢሳ ለታዳሚዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ሲዳማ የጀግኖች ምድር መሆኗንና ለየትኙም ጠላት የማይንበረከክና ከሌሎች የኢትዮጰያ ህዝቦች ጋር በመሆን ሀገርን ከጠላት ሲጠብቅ የኖረ ጀግና ህዝብ እንደሆነ በማንሳት ዛሬም የጠላትን ኃይል ቀብረን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ እውን መሆን እንረባረብ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
በሰልፋ ላይ የታደሙ የማህበረሰብ ክፍሎችም አሸባሪውን የጁንታና የተላላኪዉን ኃይል ለመመከት አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ በመሆን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ደጀን በመሆን ዘግጁ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

Leave a Reply