You are currently viewing የአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ሀገር የማፍረስ ጥምረት በውጭ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው -የጂኦ ፖለቲክስ ፕሬስ

የአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ሀገር የማፍረስ ጥምረት በውጭ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው -የጂኦ ፖለቲክስ ፕሬስ

  • Post comments:0 Comments
የአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ሀገር የማፍረስ ጥምረት በውጭ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው -የጂኦ ፖለቲክስ ፕሬስ
 
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጁት ህወሓት እና ሸኔ ሀገርን የማፍረስ ድብቅ ሴራ ሰሞኑን የምእራባውያን መገናኛ ብዙሃን አጋልጠዋል።
መንግሥት እነዚህ ሁለቱ ቡድኖች የሀገሪቱን ሠላምና አንድነት
ለማናጋት እየሰሩ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲያሳውቅ ቆይቷል።
 
እነዚህ ቡድኖች ከሰሞኑ “የኢትዮጵያን መንግስት በወታደራዊ ሀይል እናስወግዳለን” የሚል ሀገር የማፍረስ ተልእኮ መያዛቸውን በአንደበታቸው ተናግረዋል።
የእነዚህ ቡድኖች ሴራ አስመልክቶ ጂኦ-ፖለቲክስ ፕሬስ ሰፋ ያለ ትንታኔ
አውጥቷል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መንግስትን በሀይል ለማስወገድ የተስማሙበት አጀንዳ የውጭ ሀይሎች ድጋፍ እንዳለበት ጠቁሟል።
ሁለቱ የሽብር ቡድኖች በአካል መገናኘት በማይችሉበት ሁኔታ ወታደራዊ ጥምረት ፈጥረናል ማለታቸውን ያመለከተው ጂኦ ፖለቲክስ በዚህም የኢትዮጵያን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ በሚያሴሩ የውጭ አቀነባባሪዎች አማካኝነት መሆኑን አብራርቷል።
እነዚህ የውጭ አቀነባባሪዎች የሽብር ቡድኖቹ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ የጦርነት ዕቅዶችን እንዲጋሩ፣ የጋራ ስትራቴጂ እንዲነድፉና ምክር እንዲለዋወጡ እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።
ሁለቱ የሽብር ቡድኖች ከመሰሎቻቸው ጋር በመሆን ጥምረት ለመፍጠር ዕቅድ እንዳላቸው የሚጠቁመው የጂኦ- ፖለቲክስ ትንታኔ ይህም በሶሪያ “ባስማ” በሚል ፕሮጀክት የተፈጸመው አይነት አካሄድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ አብራርቷል።
የሽብር ቡድኖቹ ቀደም ሲል ከነበራቸው የተቃረነ አስተሳሰብ አኳያ እንዲሁም ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በሸኔ ላይ በወሰደው እርምጃ ምክንያት ሊግባቡ የሚችሉ አለመሆናቸውን አመልክቷል።
ይህም ቡድኖቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ከመፍጠር ያለፈ ለሀገር የሚበጅ አጀንዳ እንደሌላቸው አስረድቷል።
የማይታረቅ ግብ ያላቸው እነዚህ የሽብር ቡድኖች ባወጡት መግለጫ መሰረት የፈጠሩት ጥምረት የአጭር ጊዜ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው ዓላማቸውም የመንግስት ለውጥ ማድረግ መሆኑን ጠቁሟል።
የሽብር ቡድኖቹ አካሄድ አስከፊ ከመሆኑም በላይ ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴ መሆኑን አስገንዝቧል።

ምላሽ ይስጡ