You are currently viewing ‹‹ በአንድነት ተደራጅተን አሸባሪው ቡድን የተመኘውን ሲኦል እንዲቀላቀል ማድረግ አለብን›› – አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር

‹‹ በአንድነት ተደራጅተን አሸባሪው ቡድን የተመኘውን ሲኦል እንዲቀላቀል ማድረግ አለብን›› – አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር

  • Post comments:0 Comments
‹‹ በአንድነት ተደራጅተን አሸባሪው ቡድን የተመኘውን ሲኦል እንዲቀላቀል ማድረግ አለብን››
– አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር
 
በአንድነት ተደራጅተን አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንደተመኘው ሲኦልን እንዲቀላቀል ማድረግ አለብን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ ‹ኢትጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ቢሆን እንወርዳለን ›ሲል የሚደመጥ በመሆኑ ኢትዮጵያውያንም በተባበረ ክንድ አሸባሪው እንደተመኘው ወደ ሲኦል እንዲወርድ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለ47 ዓመታት የተካነበት መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ ህብረተሰቡ በፕሮፓጋንዳው ከመረበሽ ይልቅ፤ ጠላቱን በማወቅ፤ በሁሉም ቦታ በመደራጀት፤ መረጃ በመለዋወጥ እና የትግል ስልቶችን በመጠቀም የገባው ሀይል እንዳይወጣ እና የተመኘውን ሲኦል እንዲቀላቀል መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የጁንታውን ጠላትነት የሚያውቁት የስሚ ስሚ ሳይሆን በእያንዳንዱ ላይ በደረሰ ተግባር በመሆኑ በፕሮፓጋንዳው እንደማይታለሉና ይልቁንም ወቅቱ ይህንን አሸባሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ምድር የምናጠፋበት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ርብርብ በማድረግ የአሸባሪውን ፍጻሜ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ