You are currently viewing የደቡብ ክልል የከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በቡታጅራ ከተማ ተጀመረ

የደቡብ ክልል የከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በቡታጅራ ከተማ ተጀመረ

  • Post comments:0 Comments
የደቡብ ክልል የከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በቡታጅራ ከተማ ተጀመረ
 
የደቡብ ክልል የከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
 
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውና የክልሉ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ በመድረኩ የተገኙ ሲሆን አፋር ክልል በፈንቲ ረሱ በጋሊኮማ ጊዚያዊ መጠለያ በነበሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ በአሽባሪው ህወሃት ቡድን በተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህልና ፀሎት በማድረግ ውይይቱን አስጀምረዋል።
 
በመድረኩ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ የፓርቲ አመራሮችና የዞንና የልዩ ወረዳ አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩ በአገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምላሽ ይስጡ