የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የክተት አዋጁን ተቀብለው ወደ ጦር ግምባር መዝመታቸው ተገለፀ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማቸው አባተ የክተት አዋጁን ተቀብለው ወደ ጦር ግምባር ዘምተዋል፡፡
ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ግርማቸው አባተ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚነት በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊነትን ደርበው ሲሰሩ እንደነበር የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡
መንግስት አውጆት የነበረውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ የህወሓት የሽብር ቡድን በአጎራባች ክልሎች ላይ ወረራ በመፈፀሙ ዜጎች አገራቸውን እንዲታደጉ በቀረበው ጥሪ መሰረት ተሳትፏቸውን በተለያየ መልኩ እየገለፁ ይገኛል፡፡
የተናጠል ተኩስ አቁሙ ትላንት መነሳቱን ተከትሎም ሁሉም ኢትዮጵያዊዊ የሽብር ቡድኑ በአገር ላይ የደቀነውን ስጋት ለመቀልበስ በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡