You are currently viewing መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ ከሀሰት የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች እንዲጠበቅ ጥሪ አቀረበ

መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ ከሀሰት የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች እንዲጠበቅ ጥሪ አቀረበ

  • Post comments:0 Comments
መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ ከሀሰት የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች እንዲጠበቅ ጥሪ አቀረበ
 
መከላከያ ሚኒስቴር ህብረተሰቡ በሀሰት ከሚሰራጩ የፕሮፓጋንዳ መረጃዎች ሊጠበቅ እንደሚገባ አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያን ለማዳን እየተደረገ ያለው የህልውና ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል ።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ህብረተሰቡ መረበሽ እንደሌለበት ተናግረዋል ።
አያይዘውም በሙጃና ድልብ አካባቢ ሰርገው የገቡ የሽብር ቡድኑ ሀይሎችን የመከላከል ስራም እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ ከትክክለኛ የመንግስት አካል ብቻ ምንጩን አረጋግጦ መረጃ መከታተል አለበትም ነው ያሉት ።
በተከዜ ወንዝ በጣለው በራሱ አስክሬን መንግስት ላይ የፕሮፓጋንዳ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ቡድኑ ያደገበት የማደናገር አካሄድ አካል ነው ብለዋል ።
በተኩስ አቁም ላይ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በመከላከል ወሳኝ ተልዕኮ ላይም እንደሚገኝም አስረድተዋል።
የሽብር ቡድኑ በምዕራብ ግንባርና በአፋር በኩል ሰብአዊና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበትም ነው የገለጹት ።
ህዝቡም ኢትዮጵያን ለማዳን እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

ምላሽ ይስጡ