የህወሀት ጁንታ በግዳጅ ያሰለፋቸው ወጣቶች በአፋር እና በአማራ ክልል ከግንባር እየጠፉ እጅ እየሰጡ መሆናቸው ተገለፀ
የህወሀት ጁንታ የትግራይን ህፃናት እና ወጣቶች ያለፍላጎታቸው ከመንገድ ላይ አሰገድዶ ወደ ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን እጃቸውን የሰጡት ምርኮኞች ገልፀዋል።
ወጣቶቹ ከትግራይ የተለዩ አካባቢዎች ቤተሰቦቻቸው ሳያውቁ፣ ያለፍላጎታቸው ከመንገድ ላይ ተወስው እና የ8ቀን ስልጠና ወስደው ወደ ጦርነት መግባታቸውን ገልፀዋል።
በርካታ ሌሎች ወጣቶችም እጅ ለመስጠት በየጫካው ተበታትነው ይገኛሉ ያሉት ወጣቶቹ እጃችንን ሰጥተን በጥሩ ሁኔታ እንገኛለን ማለታቸውን የአፋር ክልል መገናኛ ብዙሀን አስታውቋል።