You are currently viewing የሀረሪ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ያደረገውን 14 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረከበ

የሀረሪ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ያደረገውን 14 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረከበ

  • Post comments:0 Comments
የሀረሪ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ያደረገውን 14 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረከበ
የሀረሪ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ያደረገውን 14 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል።
በድጋፉ ርክክብ ወቅትም ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ህብረተሰቡ ከዳር ዳር በመነቃነቅ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የሀረሪ ክልል ህዝብና መንግስትም ያደረገውን የአይነት እና የገንዘብ ድጋፎችን በዛሬዉ እለት ተረክበናል ብለዋል።
ለዚህም የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለሰራዊቱ ላበረከተው ድጋፍ እና እያሳየ ለሚገኘው አጋርነት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በሰራዊቱ ስም አመስግነዋል።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት እና በየ ደረጃው የሚገኝ የክልሉ ህዝብ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለሰራዊቱ ያለውን አለኝታነት በተግባር እየገለፀ ይገኛል።
በእለቱም በየደረጃው ከሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል እና ከሌሎች አካላት የተሰበሰበውን የ10 ሚሊየን ብር ጥሬ ገንዘብና ግምቱ አራት ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ማስረከባቸውን ተናግረዋል።
በለይም በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውስጥና ውጪ እየደረሱ ያሉ ትንኮሳዎችን እና ጫናዎችን ለመመከት የክልሉ ህዝብ በአንድነት መንፈስ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በቀጣይም በክልሉ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ነው ያነሱት።
ለውጡ እንዲመጣ የምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ህዝብ የጎላ ሚና አበርክቷል ያሉት ደሞ በብልፅግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር አስተባባሪና የሁለተኛው ዙር የክልሎች ድጋፍ አሰባሰብ አስተባባሪው ዶክተር ተመስገን ቡርቃ በአሁኑ ወቅትም ለውጡ እንዳይቀለበስ እና በሀገር ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በመሆኑም ህዝቡ እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍና አጋርነት ማጠናከርና በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ በአንድነት መመከት አስፈላጊ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

ምላሽ ይስጡ