You are currently viewing አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የጽህፈቱ አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የጽህፈቱ አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

  • Post comments:0 Comments
አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የጽህፈቱ አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
 
አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የጽህፈቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል።
አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በደም ልገሳው ወቅት ደም የለገሱበት ዋናው ምክንያት በግንባር የሀገር ደጀን በመሆን ክብር መስዋዕትነት ለሚከፍሉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው ብለዋል።
እየተሰራ ያለው ሥራ ሀገር የማደን ነው ነው ያሉት አቶ ኢስሃቅ፤ ለጁንታው ቡድን መንግስት በቶክስ አቁም ጊዜ ሰጠቶ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ የሰጠውን ዕድል አልተጠቀመም ብለዋል።
የጁንታው አስተሳሰብ ሀገሪቷን ካላስተዳደርኩ ትፍረስ አፍራሽ አስተሳሰብ ነው ብለዋል አቶ ኢስሃቅ።
በትግሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጁንታው የሚያፀዳበትና የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠናከርበት ነው ብለዋል ጽ/ቤት ኃላፊው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገሩን ለጁንታው ሽብርተኛ ኃይል አሳልፎ እንደማይሰጥ የተረጋገጠበት ሁኔታ ታይቷል ብለዋል አቶ ኢስሃቅ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንደግፍ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ዜጎች በገንዘብ፣ በሞራል፣በቁሳቁስና በህይወት ጭምር ምላሽ እየሰጡ መሆናቸውን ኩራት እንደፈጠረባቸው አቶ ኢስሃቅ ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እስከ ግንባር ድረስ ሄዶ በመሰለፍ ጭምር ለመደገፍ መዘጋጀት እንዳለባቸው ጽ/ቤት ኃላፊ አሳስበዋል።
አመራሩ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለማበርከት የወሰኑ ሲሆን ሰራተኛው ደግሞ ከ5% እስከ 50% ደመወዛቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የክልሉ ፀጥታ ኃይልን ለመደገፍ መወሰናቸው ይታወሳል።
አቶ መሀመድ አልማሂ ክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ በደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም የለገሱ ሲሆን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በገንዘብ፣ በሞራል እና በቁሳቁስ መደገፍ የዜግነት ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል።
የጽ/ቤቱ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለማበርከት የወሰኑ ሲሆን ሰራተኛው ደግሞ ከ5% እስከ 50% ደመወዛቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የክልሉ ፀጥታ ኃይልን ለመደገፍ መወሰናቸው ይታወሳል።

ምላሽ ይስጡ