ደሜን ለኢትዮጵያዬ በሚል የወጣቶች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ደሜን ለኢትዮጵያዬ በሚል የወጣቶች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

  • Post comments:0 Comments
ደሜን ለኢትዮጵያዬ በሚል የወጣቶች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
 
ደሜን ለኢትዮጵያዬ በሚል የወጣቶች የደም ልገሳ መርሃ ግብር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
 
በብልፅግና ወጣቶች ሊግ ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለው የደም ልገሳ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ወጣቱ ደሙን በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል፡፡
 
በሌላ በኩል የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት አመራሮችና አባላት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡በደም ልገሳው መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ደማቸውን የለገሱት የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት ሸሪፍ ሙሜ እንደገለጹት የሀገር ዳር ድንበርን ለመጠበቅ ደምና አጥንታቸውን መስዋዕት ለሚከፍሉ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍና ደጀን በመሆን አጋርነታችንን ለማሳየት ደማችንን እንለግሳለን ብሏል።
 
ወጣት ሸሪፍ አያይዞም ወጣቱ ትውልድ የሀገሩን ሰላምና አንድነትን በማስጠበቅ አሸባሪው የህወኃት ቡድን ሀገርን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴና በውስጥና በውጪ ሃይሎች የተደቀነብን ጫና በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ወጣቱ በአንድነት መነሳቱን ገልጾ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ደም ለመለገስ ከአምስት መቶ በላይ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ከአንድ ሺህ ዩኒት በላይ ደም እንደሚሰበሰብም ተናግረዋል።
 
በመጨረሻም የደም ልገሳ መርሃ ግብሩና ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአስተባባሪዎቹ መረዳት ተችሏል፡፡

Leave a Reply