You are currently viewing በሀረሪ መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

በሀረሪ መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

  • Post comments:0 Comments
በሀረሪ መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ
 
በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፤ የምስራቅ ዕዝ ተወካዮች ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሽኝት መርሃግብሩ ላይ ባስተላለፍት መልዕክት ወጣቶቹ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ሀገርን ለማገልገል ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወጣቶቹ ካለማንም ጫና በፍላጎታቸው መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸውም በቀጣይ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በመሆኑም ወጣቶች በስነ ምግባርና በክህሎት ራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይም በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እሴት በማክበር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ መንግስትም ለወጣቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት፡፡
መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶች እንዳሉት መንግስት የሀገር ሉዓላዊነት ለማስከበር ያደረገው ጥሪን በመቀበል በፍላጎታቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመከላከል መወሰናቸውን ተናግረዋል።
ከወጣቶቹ መካከልም ኤልያስ ያደታ “ሀገር ሲኖር ነው የሚሰራውም የሚኖረውም ሀገር ሲኖር ነው፤ በመሆኑም እኛ ወጣቶች እያለን ሀገር አትደፈርም ፤ ስለሆነም ሀገራችንን ለማዳን እና ጁንታውን ለማጥፋት ሆ ብለን ተነስተናል” ሲል ተናግሯል። በመሆኑም የሀገርን ለማዳን በቁርጠኝነት ስለመዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
ሌላው ወጣት አብዱልፈታህ መሀመድ በሰጠው አስተያየት ለሀገሬ የምቆምብት ስናፍቅ ቆይቻለሁ፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት ሀገርን ለመታደግ እድል በማግኘቴ ተደስቻለሁ ሲል ተናግሯል፡፡በዚህም የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።
መከላከያን ተከላቅያ ሀገሬን ለማገልገል በመብቃቴ ተደስቻለሁ፤ በዚህም በታማኝነት በቁርጠኝነት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ ሲል የተናገረው ደግሞ ወጣት ሄኖክ ለማ ነው፡፡
ወጣት ብሩክ ጌታቸው መከላከያን ስቀላቀል በታቅ ተነሳሽነትና በጀግንነት ስሜት ነው በመሆኑም ሀገሬንና ህዝቤን ለማገልገልና ዳር ድንበሯን ለማስከበር ተዘጋጅቻለሁ ቤተሰቦቼም መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል የወሰነውን ውስኔ እንደተቀበሉና እንዳበረታቱት ተናግሯል፡፡
በሽኝት መርሃግብሩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ፣ ም/ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ፤ የምስራቅ ዕዝ ተወካዮች ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ምላሽ ይስጡ