You are currently viewing ‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካን በራስ የመልማትአቅም ማሳያ ነው››አቅም ማሳያ ነው›› ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር

‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካን በራስ የመልማትአቅም ማሳያ ነው››አቅም ማሳያ ነው›› ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር

  • Post comments:0 Comments
‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካን በራስ የመልማትአቅም ማሳያ ነው››አቅም ማሳያ ነው›› ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር
የአድዋ ድል ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ መሰረት እንደጣለ ሁሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብም የአፍሪካን በራስ የመልማት አቅም የሚያሳይ ጠንካራ አቋም ማሳያ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ እያደረጉት ስላለው ተሳትፎ አስመልክቶ ትናንት በተሰጠው መግለጫ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ እንደገለጹት፤ የአድዋ ድል ቅኝ ግዛትን ለማሸነፍ መሰረት እንደጣለ ሁሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብም የአፍሪካን በራስ የመልማት አቅም ያሳያል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሞዴል ሆና በራሷ መቆም ስትችል የሚያስተላልፈው መልዕክት ከፍ ያለ በመሆኑ እውነታው የማያስደስታቸው ወገኖችም አሉ ያሉት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ የግድቡ ተጽዕኖ ከሱዳንና ግብጽ ጋር ብቻ የተያያዘ ስላልሆነ ዝግጅታችንና አስተሳሰባችን ያንን ሊያሸንፍ በሚችል ደረጃ መሆን ይገባል ብለዋል።
የግድቡን ደህንነት ለመጠበቅና ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማልበስ በዚህ ዓመት ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ያስታወሱት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ እስካሁን ድረስ 75 በመቶ የሚሆነው ችግኝ መተከሉን አስታውቀዋል፡፡
ለግድቡ እየተደረጉ ያሉ ሁለንተናዊ ድጋፎች አበረታች መሆኑን ያስታወቁት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ