መቀመጫውን ሲውዘርላንድ ያደረገው እኔም ለወገኔ ማህበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በከፍተኛ ገንዘብ የቦንድ ግዢ እየተፈጸመ እንደሚገኝ ተጠቆመ፡፡
ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ያቀፈው ማህበሩ፣ ከተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና በጽኑ በመቃወም ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
ከውጭም ከውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሉአላዊነት እና ለራሳቸው ህልውናም ጭምር በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በሲውዘርላንድ የሚኖሩና እኔም ለወገኔ በተሰኘ ማህበር የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድቡ የቦንድ ግዢ በመፈጸም ጫናውን ለመቋቋም የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል፡፡
ታላቁ ህዳሴ ግድብ የህልውና ጉዳይ ነው የሚሉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰአት መከፋፈልን ወደ ጎን ብለን ለሀገራችን ሉአላዊነት ከውስጥም ከውጭም በጋራ መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
ለሀገራቸው ታላቅ ተጋድሎ የሚያደርጉ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ ለእኩይ አላማ የተሰለፉ ዲያስፖራዎች መኖራቸው ቢታወቅም ለመልካም ስራ የተሰለፍን ግን ቁጥራችን ብዙ ነው ብለዋል፡፡
ማህበሩ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡