ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቶች የታደለች አገር ናት፡፡ የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በማልማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮቻችንን መፍታት ህጋዊ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ መብታችንም ጭምር መሆኑን አለም ሊገነአብልን ይገባል፡፡
አገራችንን በተላያዩ አቅጣጫዎች የዲፕሎማሲ ጫና ውስጥ በማስገባት የተፈጥሮ ሃብቶቿን ለልማቷ እንዳትጠቀምም ሆነ የራሷን ችግሮች በራሷ እንዳትፈታ የሚደረገው ያልተገባ እንቅስቃሴ እኛ ኢትዮጵያዊያንን ይበልጥ ያጠናክረን እንደሆን እንጂ ለአፍታም ቢሆን ከጉዟችንና ከግባችን አያስቆመንም፡፡
የአባይ ግድብ የኢትዮጵያዊነት አሻራችን፣ የጋራ ማንነታችን መገለጫና የዛሬውና የመጪው ትውልድ የጋራ ሃብት ነው፡፡ ግድቡን በፍጥነት አጠናቀን ለታለመለት አላማ በማዋል መጪውን ትውልድ በጽኑ መሰረት ላይ መገንባት ይጠበቅብናል፡፡ የዘንድሮውን የግድቡን የውሃ ሙሌትም በስኬት ማጠናቀቅ የሁላችንንም ርብርብ ይፈልጋል፡፡
የምንገነባት ኢትዮጵያ በህዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተች ጠንካራ ህብረ ብሄራዊት አገር ነች፡፡ ወንድማማችነትን፣ አብሮነትንና የጋራ ብልጽግናን የሚጎዱ ማናቸውንም ሃይሎች አጥብቀን በመታገል ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በጠንካራ መሰረት ላይ እንገነባለን፡፡
የውጭ ህሎችን ጫና ለመመከትም ሆነ ጠንካራ ህብረብሄራዊ አንድነትን ለመገንባት የውስጥ ችግሮቻችን እንቅፋት ሊሆኑብን አይገባም፡፡ ምንም አይነት ልዩነት ቢኖረን በውይይት፣ በክርክርና በልሂቃን ድርድር ልዩነቶቻችንን በማስታረቅ በአገራዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተባብረን በጋራ በመስራት የአገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አለብን፡፡
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ